Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ ለክልል ግዥ ተቆጣጣሪ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

(መስከረም 20/2019 ዓ.ም| አዲስ አበባ)– የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በመንግስት ግዥ ስርዓት ውስጥ ቁጥጥርን፣ ህግ አክባሪነትን እና የስነ-ስርዓት ትክክለኝነትን ለማጠናከር ለክልል ግዥ ተቆጣጣሪ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምኒሊክ ሳሙኤል የመንግስት ግዥ በሀገር ግንባታ ውስጥ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሚና አብራርተዋል። አቶ ምኒሊክ አክለውም የስልጠናው ዋና ዓላማ የአሰራር ክፍተቶችን መለየት፣ ከፈተናዎች መማር፣ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ እና የህግ ተገዥነትን ማስፈን መሆኑን ጠቅሰው ተሳታፊዎች መድረኩን ለልምድ ልውውጥ እና ለጋራ ተግባቦት እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

የመክፈቻ ንግግሩን ተከትሎ የባለስልጣኑ የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጸጋዬ አበበ በህጋዊነት ኦዲት (compliance auditing) ላይ ገለጻ አቅርበዋል። አቶ ጸጋዬ በማብራሪያቸው ጥብቅ የኦዲት አሰራር የህዝብን እምነት ለማጠናከር፣ ብልሹ አሰራርንና የጨረታ ማጭበርበርን ለመከላከል እንዲሁም የመንግስት ገንዘብ ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኝ ለማስቻል ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ሰዓት በባለስልጣኑ የክዋኔ እና ህጋዊነት ኦዲት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስ ጎዳና በኦዲት ክንውንና በተሳታፊዎች ሚና ላይ ገለጻ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ስልጠናው ነገም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *