Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ የመጀመሪያውን ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ገመገመ።

(ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም| አዲስ አበባ)– የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ተቋማዊ ስራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ አካሄደ።

የውይይት መድረኩን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በንግግር የከፈቱ ሲሆን በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም፣ የዲጂታላይዜሽን እና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስራዎችን በውጤታማነት ለማስቀጠል የሩብ ዓመቱን አፈጻጸም በቅርበት መገምገም እና ክፍተቶችን ማረም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የባለስልጣኑ ስኬት የሁሉም ሰራተኛ ስኬት በመሆኑ ሁሉም በተመደበበት የስራ ቦታ ውጠጤታማ ስራ ማከናወን እንደሚገባው ያመላከቱት ዋና ዳይሬክተሯ በምንሰራቸው ስራዎች በተቋማት ላይ ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል ብለዋል።

በመድረኩ አቶ መስፍን መኮንን የተቋሙን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። ሪፖርቱ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ አበይት ተግባራት፣ የኤሌክትሮኒክ የመንግስት ግዥ (e-GP) ስርዓት ትግበራ ስፋት፣ የህግና የአሰራር ማሻሻያዎች እንዲሁም ያጋጠሙ ፈታኝ ሁኔታዎችንና የተገኙ ስኬቶችን በዝርዝር ያካተተ ነበር።

የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመስርተው በጥንካሬ የታዩ አሰራሮችን ለማጽናትና ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችሉ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳት የውይይቱ አካል አደርገዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ የሩብ ዓመታት የታቀዱ ግቦችን በብቃት ለማሳካት፣ የስራ ባህልን ለማጎልበት እና የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ቀልጣፋና ግልጽ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተሰጥተው ዉይይቱ ተጠናቋል።

#የመንግስትግዥና ንብረት ባለስልጣን #FPPPA

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *