Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ የ7ኛውን ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ንቅናቄ አስመልክቶ ለአመራሮቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

(ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም|አዲስ አበባ) – የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን 7ኛውን ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ንቅናቄን በማስመልከት ለአመራሮችና ለሥራ ሃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው በብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ባለሙያዎችን የቀረበ ሲሆን በዋናነትም የሳይበር ደህንነት የህልውና ጉዳይ እንደሆነና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከሚያስገኛቸው ትላልቅ እድሎች ጎን ለጎን ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን መከላከል እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ መክፈቻ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዋና ዳይሬክተሯ በባለስልጣኑ የተጀመሩ የዲጂታል ለውጥ ሥራዎች ማለትም (e-GP) ሥርዓት፣ የዲጂታል የንብረት አስተዳደር እና የመረጃ ማዕከላዊ አያያዝ የሀገሪቱን የሕዝብ ሀብት፣ የግዥ መረጃዎችና የአቅራቢዎችን መረጃ የያዙ በመሆናቸው ደህንነታቸውን መጠበቅ የሁሉንም ሠራተኛና አመራር የጋራ ኃላፊነት እንደሆነ አሳስበዋል። አያይዘውም አመራሮች የተቋሙን የመረጃ ደህንነት ፖሊሲዎች በማስፈጸም፣ ለደህንነት ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት በመስጠትና የደህንነት ባህልን በምሳሌነት በመምራት ረገድ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በስልጠናው ማዕቀፍ ውስጥ በሀገራችን የሳይበር ደህንነት ስጋት ያለባቸው ከባቢዎች፣ የሳይበር አንድምታዎች፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ሳይበር፣ የጥቃት ዓላማዎች፣ የሳይበር አደጋዎችን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች እንዲሁም የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሳይበር ጥቃት ኢላማ የሚሆንባቸው ምክንያቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመጨረሻም የኢጂፒ (e-GP) ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ያፌት መኮንን እንደገለጹት ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአንድ ቀን ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ቀጣይነት ያለው እና ሁሉንም ባለሙያዎች ባካተተ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *