Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

News

ባለስልጣኑከፌዴራልባለበጀትመስሪያቤቶችሃላፊዎችጋርውይይትእያካሄደነው።

(ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከአሰራር ስርዓት ማዘመን፣ ከዲጂታላይዜሽን እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ አበይት የሪፎርም ስራዎችን አስመልከቶ ከፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ፈቃዱ ሆረታ እንደገለጹት፤ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን በርካታ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን አከናውኗል። ተቋሙ የመንግስት የኤሌክትሮኒክ  ግዥ (e-GP) ስርዓትን በፌዴራል ደረጃ ሙሉ በሙሉ ከመተግበሩ ባሻገር አሰራሩን ወደ ክልሎች ለማውረድ ሰፋፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ክቡር አቶ ፈቃዱ አክለውም ባለስልጣኑ ከመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) ስርዓት በተጨማሪ የበይነ-መረብ ትምህርት (e-Learning)፣ የተሽከርካሪ ስምሪትና ነዳጅ አጠቃቀም ቁጥጥር (e-Fleet) እና  ሌሎች የዲጂታል ስራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ስራ ላይ እንዳዋለ አመላክተዋል።

ከዲጂታላይዜሽን በተጨማሪ ባለስልጣኑ ውጤታማ የኦዲትና ክትትል ስራዎችን፣ የይግባኝና ጥፋተኝነት ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን እንዲሁም የመንግስት አገልግሎት የሪፎርም ስራዎችን በላቀ ሁኔታ እያከናወነ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ክቡር አቶ ፈቃዱ በመድረኩ ላይ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሰራሩን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ብዙ ስራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰው በመድረኩ ላይ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሪፎርም እና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ ዘላቂነት ያለው የግዥ ስርዓት ስትራቴጂክ እቅድ (Sustainable Procurement) እና አደገኛ ቆሻሻዎች አያያዝ፣ አጠባበቅ፣ አጓጓዝ እና አወጋገድ ማኑዋል ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው አመላክተዋል።

በአሁኑ ሰዓት የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የኢጂፒ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ያፌት መኮንን ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን ውይይቱ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚቀጥል ይሆናል።

ባለስልጣኑ ከሲዳማ ክልል ለተውጣጡ አመራሮች የሪፎርም ትግበራ ልምዱን አካፈለ።

(ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን ከሲዳማ ክልል ለተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች የተቋሙን የአስተዳደርና አገልግሎት ማሻሻያ ሪፎርም አተገባበር ልምድ እና ያገኛቸውን በጎ ውጤቶች አካፈለ።

በመድረኩ ላይ የሪፎርም አፈጻጸም ሰነዱን ያቀረቡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት ተቋሙ የሪፎርሙን የትግበራ ጊዜን በውጤታማነት እየተወጣ የሚገኝ የገለጹ ሲሆን አሁን ላይ የተገኘውን ስኬት ወደ ማጽናት ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ሰፋፊ ተግባራትን እያከናወነ አብራርተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ባለስልጣኑ በተለይም የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት፣ ተቋማዊ አደረጃጀትን በማስተካከል፣ የሰው ሀይልን በብቃት ማበልጸግ እና አሰራሮችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ ረገድ ጠንካራ እና ለዋጭ ስራዎችን ማከናወኑን ጠቁመዋል።

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ የሪፎርም ትግበራው ዋና ዋና አፈጻጸሞች እና የተገኙ ውጤቶችን በተለይም የህግ ማዕቀፎች እና የአሰራር ስርዓት ማሻሻያን በገለጹበት ገለጻ አዲሱን የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1333/2016 መነሻ በማድረግ የግዥ አፈጻጸም፣ የመድኃኒትና ህክምና መሳሪያዎች፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች እና የንብረትና ተሸከርካሪ አስተዳደር መመሪያዎች ተዘጋጅተው በስራ መዋላቸውን እና የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የጨረታ መደበኛ ሰነዶች (SBD)፣ የአቤቱታና ይግባኝ አቀራረብ ማንዋሎች እንዲሁም ዘላቂነት ያለው የግዥ ስርዓት (Sustainable Procurement) ማንዋል ተዘጋጅተው ስራ ላይ እንደዋሉ አመላክተዋል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኤሌክትሮኒክ የመንግስት ግዥ (e-GP) ስር ዓት ትግበራ፣ የተሸከርካሪ ቁጥጥር እና ንብረት ቁጥጥር (e-Fleet) እና ሌሎች ዲጂታል ስራዎችን በከፍተኛ ዲስፕሊን እየተገበረ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

ባለስልጣኑ የሪፎርም ውጤታማነቱን ለማስቀጠል የሰው ሀይል ብቃትን ማሳደግ እንዲሁም ብዝኃነት እና አካታችነት መተግበር አስፈላጊ በመሆኑ ሰራተኞችን የማብቃትና አካታችነቱን እንዲጠብቅ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተብራርቷል።

በቀጣይም ባለስልጣኑ እስካሁን ያገኛቸውን የዲጂታላይዜሽን እና የተቋማዊ ሪፎርም ስኬቶች በማጠናከር፣ የዲጂታል አሰራሩን ወደ ሁሉም ክልሎች የማስፋፋት፣ የአገልግሎት ጥራትን የማሳደግ እና ግልጽና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን የመገንባት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን የሲዳማ ክልል አመራሮችም ባለስልጣኑ እየተገበረ በሚገኘው የሪፎርም ስራ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄዱ::

(ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም)፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ማዕቀፍ ውስጥ በመሳተፍ በዛሬው እለት  የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በክረምት ወቅት ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ቀደም ሲል የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አንዱ ሲሆን በዛሬው እለት የተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብርም የዚህ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል እና የቀጣይ በጎ አድራጎት ስራዎች ማስቀጠያ መርሃግብር ነው።

በቀጣይ የክረምት ወራትም ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የበጎ አድራጎት መስኮች ላይ ተሳትፎውን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። በተለይም የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስና መገንባት፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት፣ ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞችን የምግባ መርሃግብር ማካሄድ እና ሌሎች መሰል ህብረተሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ለማከናወን ዝግጅቶች ተጠናቀው እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።   

የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የሚያሳዩት ንቁ ተሳትፎና ተነሳሽነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚቀጥል ይሆናል።

በኮንትራትማኔጅመንትዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠናተጠናቀቀ።

(ሀምሌ 11/2018 ዓ.ም)፣ በኮንትራት ማኔጅመንት (ውል አስተዳደር) ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ሀገር አቀፍ የስልጠና መድረክ በስኬት ተጠናቋል። በድረኩ ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቅሌ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው በዘርፉ ያሉ የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት እና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የገጠር መንገድ ፕሮጀክቶች የህዝብን ህይወት የሚቀይሩ መሰረታዊ የልማት ፕሮግራሞች መሆናቸው፣ የኮንትራት ማኔጅመንት አሰራርን ማዘመን እና ከጨረታ ሰነድ ዝግጅት መጀመር አስፈላጊ መሆኑ፣ የዋጋ ማሻሻያ (Variation Order) እና የጊዜ ማራዘሚያ (Time Extension) ቁጥጥር አስፈላጊ መሆኑ፣ የፕሮጀክት ጥራት ቁጥጥር እና የተቋማት ቅንጅት ለማንኛውም ስራ ስኬት መሰረት መሆኑ፣ የግዥ ህግ ልማትን እንደማያደናቅፍ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል።

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በማጠቃለያቸውም ከዚህ ስልጠና የተገኙ እውቀቶችና የጋራ ተሞክሮዎች ወደ ስራ ሲመለሱ በሚገባ ሪቪው (Review) ሊደረጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። የስልጠናውና የሁለት ቀኑ ውይይት ትክክለኛ ውጤት ሊለካ የሚችለው በስራዎች ጥራት፣ የፕሮጀክት መዘግየት ጊዜ ሲቀንስ፣ የተሻሻለ የኮንትራት አስተዳደር ሲኖር እና በተቋማት ቅንጅት አማካኝነት የህዝባችንን እርካታ ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ በመሆኑ ሁሉም አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።