Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ሲካሄድየነበረውሀገራዊየግዥናንብረትአስተዳደርየምክክርመድረክበከፍተኛግብዓትናበውጤታማነትተጠናቀቀ።

ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም)፦ የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በቢሾፍቱ ከተማ ሲያካሂደው የነበረው በተሻሻለው የመንግሥት ግዥና ንብረት አዋጅ፣ የአሠራር መመሪያዎችና የዲጂታል ሥርዓቶች ዙሪያ ያተኮረው ሀገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የምክክር መድረክ በተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም በከፍተኛ ግብዓትና በውጤታማነት ተጠናቋል።


በመድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት የግዥና ንብረት ውጤታማነትን ለማሳደግ የአሰራር ስርዓትን ማዘመን እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ አሠራር በመዘርጋት የሕዝብና የሀገርን ሀብት በግልጽነትና በተጠያቂነት መምራት እያስቻለ እንደሚገኝም አመላክተዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት አክለውም የተያዘውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ከተናጠል አቅም አልፈው እውቀትና ልምድን በመደመር እሳቤ በማቀናጀት በጋራ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ በባለሥልጣኑ የግዥና ንብረት ማሻሻያና አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ አማካኝነት በተሻሻለው የግዥ ሕግ ማዕቀፍ እና በቁልፍ የግዥ አመላካቾች ላይ ሰፊ ገለጻ የቀረበ ሲሆን ባለሥልጣኑ እየተተገበራቸው የሚገኙ የኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) እና መሰል ዲጂታል ሥራዎችን አስመልክቶ በባለሥልጣኑ የኢጂፒ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ያፌት መኮንን ዝርዝር ገለጻ ቀርቧል።

የቀረቡ ገለጻዎችን ተከትሎ ከክልልና ከከተማ መስተዳድሮች የገንዘብ ቢሮ፣ የግዥና ንብረት ባለሥልጣን ቢሮ እንዲሁም ከተለያዩ የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት መስጫ ቢሮዎች የተወከሉ አመራሮችና ባለሙያዎች የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል። በተለይም የሕግና አሠራር ማዕቀፎች ቅንጅት፣ የዲጂታል ግዥ ማስፋፋትና የቴክኖሎጂ ዝግጁነት ብሎም የአቅም ግንባታና የሙያ ብቃት ጉዳዮች በስፋት የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።   ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በባለሥልጣኑ አመራሮች በኩል ተገቢው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ መድረኩ የተነሱትን ግብዓቶች በማካተት፣ በቀጣይ የጋራ አቅምን በመገንባት፣ የዲጂታል አሠራርን በማስፋፋት፣ የአፈጻጸም ክትትልና ተጠያቂነትን በማጠናከር ረገድ የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *