Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

የገንዘብ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

ሐምሌ 27 ቀን 2018 . (አዲስ አበባ) የገንዘብ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የ2018 ዓ.ም. የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በቱሉ ዲምቱ አካባቢ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

የዕለቱን መርሐ-ግብር ያስጀመሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ባደረጉት ንግግር ባለፉት ስምንት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ስኬታማ በሆነ መንገድ ሲከናወን መቆየቱንና በየዓመቱ የሚተከለውም የችግኝ መጠን እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህ እንቅስቃሴ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ከመሆኑም በላይ የአካባቢ የደን መራቆትን በመከላከል የሀገሪቱን የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ማገዙን ጠቁመዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም መርሐ-ግብሩ በየዓመቱ በተደራጀ የሕዝብ ተሳትፎና አቅም የሚከናወን በመሆኑ ከፍተኛ የበጀት ቁጠባ ማስገኘቱን አብራርተዋል። በተለይም እንቅስቃሴው የደን ሽፋንን ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ፣ የአፈርና የውኃ ሀብትን ለመጠበቅ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ አረንጓዴና ጤናማ አካባቢን ለማስረከብ የሚያስችል ብሔራዊ ንቅናቄ መሆኑን አግንነዋል።

በመጨረሻም የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ይህን ብሔራዊ ንቅናቄ በመደገፍ በቀጣይም የአካባቢ ጥበቃን፣ የአረንጓዴ ልማትንና የዘላቂ ልማት ግቦችን የሚያግዙ ተግባራትን በቁርጠኝነት እንደሚያስቀጥሉ ያረጋገጡ ሲሆን የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም ንቁ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ 7000 ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን የሚያከናውን ይሆናል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *