የዘላቂ የመንግስት ግዥ ዋና ዋና መርሆች (principles of sustainable procurement) ምንድን ናቸው?
ዘላቂ የመንግስት ግዥ የሚመራባቸው በርካታ መርሆች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ፦
ግልጽነት (Transparency)፦ የሚከናወኑ የግዥ ሂደቶች ለሁሉም ተሳታፊዎች ግልጽ እና ክፍት መሆን አለባቸው። ግልጽነት ሙስናን ይቀንሳል በምትኩ የህዝብን እምነት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና አለው።
ተጠያቂነት (Accountability)፦ ግዥውን በበላይነት የሚመሩት ሀላፊዎችም ይሁኑ ግዥውን የሚፈጽሙት ባለሙያዎች በግዥ ውሳኔዎች እና በግዥ ክንውኖች ላይ ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል፤ በተለይም የተቋም የበላይ ሀላፊዎች የመንግስት ሀብት በብቃት እና በተፈለገው መንገድ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
ፍትሃዊ ውድድር (Fair Competition)፦ ሁሉም አቅራቢዎች/ተጫራቾች ለመንግስት ውሎች ለመወዳደር እኩል ዕድል ሊኖራቸው ይገባል።
ለተከፈለው ገንዘብ ተመጣጣኝ ዋጋ (Value for Money)፦ ዘላቂነት ያለው የመንግስት ግዥ ትኩረት በዝቅተኛው የመግዣ ዋጋ ብቻ ሳይሆን በሙሉ የህይወት ዑደት ወጪ (whole-life costing) ላይ የሚያተኩር በመሆኑ የሚከናወነው ግዥ ይህን መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል።
የአካባቢ እና ማህበራዊ ኃላፊነት (Environmental and Social Responsibility)፦ የግዥ ውሳኔዎች እና የሚከናወኑ ግዥዎች በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የሚወንሱ እና ማህበራዊ ጥቅሞችን ማሳደግ የሚችሉ አለባቸው።

0 Comments