የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄዱ::

(ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም)፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ማዕቀፍ ውስጥ በመሳተፍ በዛሬው እለት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በክረምት ወቅት ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ቀደም ሲል የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አንዱ ሲሆን በዛሬው እለት የተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብርም የዚህ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል እና የቀጣይ በጎ አድራጎት ስራዎች ማስቀጠያ መርሃግብር ነው።
በቀጣይ የክረምት ወራትም ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የበጎ አድራጎት መስኮች ላይ ተሳትፎውን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። በተለይም የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስና መገንባት፣ የመማሪያ ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት፣ ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞችን የምግባ መርሃግብር ማካሄድ እና ሌሎች መሰል ህብረተሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ለማከናወን ዝግጅቶች ተጠናቀው እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።
የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የሚያሳዩት ንቁ ተሳትፎና ተነሳሽነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚቀጥል ይሆናል።







0 Comments