Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

የመንግስትግዥናንብረትባለስልጣንለመቄዶኒያአረጋውያንናአዕምሮህሙማንማዕከልማዕድአጋራ።

(ሀምሌ 22/2018 .ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በክረምት ወራት ከሚያከናውናቸው የበጎ አድራጎት ተግባራት አካል የሆነውን የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር በመቄዶኒያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መረዳጃ ማዕከል በመገኘት በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አከናወኗል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዚህ የበጎ አድራጎት መርሃ ግብሩ ለ1,000 የሚሆኑ የማዕከሉን አባላት የምገባ አገልግሎት በማካሄድ ለአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ በየአመቱ በሚያካሂደው በጎ ተግብር የተነሳ ቀደም ሲል ሀምሌ 23 በመቄዶኒያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን ማዕከል የባለስልጣኑ ቀን ተብሎ የተሰየመ ቀን ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በ2018 በጀት ዓመት 347,491 ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

በበጎ አድራጎት መርሃ ግብሩ ላይ በአካል ተገኝተው ህሙማኑንና አረጋውያኑን ያበረታቱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደተናገሩት የማዕድ ማጋራት ዝግጅቱ ለወገኖቻችን ያለንን ጥልቅ አክብሮትና ፍቅር ለመግለጽ የተደረገ ነው ብለዋል። አያይዘውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁሌም ቢሆን ድጋፍና እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ወገኖች ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም “ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው” በሚል ጥልቅና ሰብአዊ መርህ በርካታ አረጋውያንና አዕምሮ ህሙማንን በማስጠለልና በመንከባከብ ላይ የሚገኘው መቄዶኒያ ትልቅ ሀገራዊና ሰው-ተኮር አገልግሎት የሚሰጥ አንጋፋ ድርጅት በመሆኑ እንዲህ ባሉ ቦታዎች ተገኝቶ አቅመ ደካሞችን መጠየቅና ማበረታታት የሁሉም አካል ሀገራዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በዛሬው ዕለት ባከናወነው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ብቻ የማይወሰን ይልቁንም በቀሪዎቹ የክረምት ወራት የተጀመሩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን  እንዲህ አይነቱ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ተቋሙ ለህብረተሰብ አገልግሎት የሚሰጠውን ትኩረትና ሰብአዊ እሴት በተግባር የሚያሳይበት አወንታዊ እርምጃ ነው።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *