Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ የግዥ ኦዲትን እና የቁልፍ የግዥ አመላካቾችን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ በትጋት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት የግዥ ኦዲትን እና የቁልፍ የግዥ አመላካቾችን በሚመለከት ከክልል የግዥና ንብረት እንዲሁም ከፋይናንስ ሀላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂድዷል፡፡

የግዥ ኦዲትን በሚመለከት የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለልስጣን የመንግስት ግዥና ንብረት ክዋኔና ህጋዊነት ኦዲትና ክትትል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስ ጎዳና ሲሆኑ ኦዲት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ዋጋ እንዲያስገኝ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት መንገድ እንደሆነና በጥብቅ ስነ፟ ምግባር መከናወን እንዳለበት አብራርተዋል፡፡

አቶ አዲስ በገለጻቸው የኦዲት ዋና ዓላማ ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን ማሳደግ፣ ሕገወጥነትን፣ ማጭበርበርን እና ሙስናን መከላከል፣ ህጎችን እና መመሪያዎችን መከበራቸውን ማረጋገጥ፣ የውስጥ ቁጥጥርን ማጠናከርና የስጋት ከባቢን መቀነስ እንዲሁም ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ማስቻልና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ ሲሉ አክለዋል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኦዲት ስራ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው ያሉት አቶ አዲስ ማንኛውም የኦዲት ባለሙያ የኦዲትን መርህ ተከትሎ ማከናወንም እንዳለብት አመላክተዋል፡፡ እንደ አቶ አዲስ ገለጻ አንድ ኦዲተር ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ተጠያቂነትን የተላበሰ፣ ታማኝነት እና ምስጉን ስነ ምግባር ያለው እና የኦዲት መርሆን መከተል ይኖርበታል ብለዋል፡፡

አቶ አዲስ በማጠቃለያ ገለጻቸው በ2017 በጀት ዓመት የታዩ የኦዲት ግኝቶችን ለተወያዮች ያቀረቡ ሲሆን የቀጣይ የእርምት አቅጣጫዎችንም ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱ ከግዥ ኦዲት በተጨማሪ በቁልፍ የግዥ አመላካቾች ላይ በአቶ እሸቱ አጥናፉ እና በአቶ ጸጋዬ አበበ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ምላሽና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *