ባለስልጣኑ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምገባ መርሐግብር አከናወነ።

(ሚያዝያ 04/2018)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል በመገኘት ከ200 በላይ ለሚሆኑ ለአቅመ ደካማ የማሕበረሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራት የትንሳኤን በዓልን በጋራ አክብረዋል።
በምገባ መርሃግብሩ ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት በዓሉን ስናከብር የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንና አቅመ ደካሞችን በማሰብ መሆን እንዳለበት ገልጸው በተለይም እንዲህ አይነት ቦታዎች ላይ በመገኘት ፍቅርንና አንድነትን ማጋራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳየበት እንደመሆኑ ዕለቱን ተደጋግፎና ተረዳድቶ በማሳለፍ የክርስቶስን ዓላማ ማሳየት እንደሚገባ ያስገነዘቡ ሲሆን እንዲህ አይነት ሰው ተኮር ተግባራት ወደፊትም ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።





0 Comments