ባለስልጣኑ የሰንደቅአላማን ቀን በድምቀት አከበረ።

(ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም) የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የሰንደቅ አላማ ቀን ከእቅድና ፕላን ሚኒስቴር እንዲሁም ከመንግስት ግዥ አገልግሎት ጋር በመሆን በድምቅት አክብሯል።
የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ማንሰራራት አዲስ ዘምን ድል ብሥራት፣ የኅብረብሔራዊነታችን እና የአብሮነታችን የታሪክ ማብሰሪያ ዓርማ፣ ለኢትዮጵያ ሕዳሴ፣ የጀግንነታችንና የአያበገሬነታችን መገለጫ፣ የነፃነታችን ማማ፣ ለኢትዮጵያ ዐዲስ ዘመን ከፍታ፣ የዘመናት የነጻነታችንና የሥልጣኔያችን አብሪ ኮከብ፣ የሕዳሴያችን ሕያዊ ምስክር፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነታችን መገለጫ፤ የሀገራችን ታላቅነት ማብሰራያ፣ የብልፅግናችንና የሐገራዊ ከፍታችን ብርሃን ማሳያ፣ ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ ቆራጥ አመራር ፈተናዎችን አሸንፋ ትሻገራለች በሚሉ መልዕክቶች ደምቆ እየተከበረ ይገኛል።


0 Comments