Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ድጋፍ አደረገ።

(መጋቢት 11/2018 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ በቦታው በመገኘት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ድጋፍ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በጋሞ ዞን አስተዳደር ተገኝቶ ሀዘኑን የተጋራ ሲሆን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ500,000 ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የምግብ ዱቄት አበርክቷል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት የተሰማቸው ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች መጽናናትን ተመኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *