Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ ለግዥ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ስልጠና (professionalization Training) በሚሰጥበት እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

(መጋቢት 10/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተቋማት ግዥ ባለሙያዎችን አቅም አጎልብቶ የግዥና ንብረት ጥራትና ቅልጥፍናን ለመጨመር እና የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ለማስቻል የህግ መዕቀፎችን ከማሻሻል ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የግዥና ንብረት ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት በተለይም አጫጭር ስልጠናዎችን እና ድጋፎችን እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የፌዴራል የግዥ ባለሙያውችን ብቃት ለማሳደግ የሙያ ብቃት ስልጠና (professionalization Training) ለመስጠት ቀደም ብሎ  ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨስሪቲ ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት መሰረት ስልጠናውን ለማስጀመር በሚያስችላቸው እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ከእቅድ በተጨማሪ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተዘጋጁት የስልጠና ሞጁሎች ላይ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨሲሪቲ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው ዲጂታል የግዥና ንብረት ስርዓትን ለማጠናከር ስልጠናው ተግባር ተኮር መሆን እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የባለሙያዎችን በቃት በማሳደግ በኩል የራሱን ሚና እንደሚወጣ በውይይቱ ተገልጿል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *