ባለሥልጣኑ የአስተዳደርና አገልግሎት ማሻሻያ ሪፎርም አፈጻሰም ላይ ከሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

(ሀምሌ 17/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በአስተዳደርና አገልግሎት ማሻሻያ ሪፎርም የትግበራ ምዕራፍ አፈጻጸም ሪፖርት ሰነድ ላይ ከሠራተኞች እና ከሥራ ክፍሎች ኃላፊዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
በውይይት መድረኩ ላይ የሪፎርም አፈጻጸም ሰነዱን በአቶ መላኩ ተጓዴ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ ላይም በዝርዝር ውይይት ተደርጎበታል:: ሰነዱ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በህግ ማዕቀፎች ማሻሻያ፣ በሰው ሀብት ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በዲጂታላይዜሽን (e-GP እና e-Fleet Management) ዘርፎች ያከናወናቸውን አበይት ተግባራትና ያስመዘገባቸውን ውጤቶች የሚያሳይ ነው::
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የቀጣይ ሥራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል:: ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በንግግራቸው የተጀመሩ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ተቋሙ የተቀመጡትን ስትራቴጂካዊ ግቦች እንዲያሳካ የመላው ሠራተኛና አመራር የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን አሰምረውበታል።




0 Comments