Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ለባለስልጣኑ አመራር ስልጠና ተሰጠ።

(መጋቢት 12/2018 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ለአመራሮች ብዝሃነትን ማስተዳደር  እና የአካቶ ትግበራ ላይ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናውን የሰጡት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት መልሰው ደጀኔ (ዶ/ር) እንደገለጹት ብዝሃነት ከማህበራዊ፣ ከቋንቋ፣ ከአስተሳሰብ፣ ከጾታ፣ ከባህል እና መሰል ጉዳዮች ጋር ሊታይ የሚችል ሲሆን ብዝሃነትን መቀበልና በአግባቡ ማስተዳደር መቻል ስኬትን ለማብሰር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

እንደ ዶ/ር መልሰው ገለጻ ብዝሃነትን መቀበል፣ ማክበርና ማስተዳደር ውጤታማ የስራ ባህል እንዲዳብር እና ጠንካራ የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲፈጠር በማድረግ የተቋም ግብ እንዲሳካ የሚኖረው ሚና የጎላ ነው።

ዶ/ር ደጀኔ አክለውም ብዝነትን መቀበልና ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተቋማት ውስጥ አካታችነትን መተግበር መቻል ሀገርን የሚመስል ተቋም ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽዖ እንዲሚኖረው የገለጹ ሲሆን ይህን በውጤታማነት ለመተግበር የተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ያላቸው ሚና አይተኬ መሆኑን አመላክተዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ብዝሃነትንና ማህበራዊ አካቶን በሚመለከት በባለስልጣኑ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት ባለስልጣኑ ብዝሃነትን ያከበረና አካታችነትን በህግና በአሰራር ስርዓት ሳይቀር አካትቶ እየተገበረ እንደሚገኝ ገለጸዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት ሲያብራሩ ባለስልጣኑ ማህበራዊ አካትቶን በሚመለከት የግዥና ንብረት አዋጁን በብሬል ከማሳተም ጀምሮ የስርዓተ ጾታ እና ማህበራዊ አካትቶ ትግበራ ማኑዋል አዘጋጅቶ እየተገበረ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ በግዥና ንብረት አዋጁ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአነስተኛ እና ጥቃቅን አምራቾች ልዩ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ ድንጋጌ መኖሩንም አብራርተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *