Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

News

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዢ ስርዓትን ለመተግበር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ርዕሰ መስተዳደሩ ገለጹ፡፡

(ሚያዝያ 25/2018 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የግዥና ንብረት ስርዓቱን አዘምኖ የመንግስት ገንዘብ ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኝ ለማስቻል ከሚተገብራቸው ዲጂታል ተገባራት አንዱ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት (e-GP System) ሲሆን ስርዓቱን በሁሉም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ከማስተግበር ባሻገር ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች እንዲተገብሩት ለማስቻል ውይይት እያደረገ፣ ስልጠና እየሰጠና የክልልና የከተማ መስተዳደሮች የግዥና ንብረት ህጎች ከፌዴራሉ የግዥና ንብረት ህጎች ጋር እንዲጣጣሙ እገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህም  ባለስልጣኑ በዛሬ እለት ከሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስርዓቱን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የፌደራል የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ሲሆኑ ኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ስርዓት የግዥ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ያደረገ በመሆኑ ተወዳዳሪን የሚጨምር፣ አሳታፊ፣ ከገጽ ለገጽ ግንኙነት የጸዳ በመሆኑ ብልሹ አሰራሮችን የሚቀንስ፣ ወጪ ቆጣቢ ብሎም የህግ መከበርን የሚያረጋግጥ ስርዓት ነው ብለዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መሰረት አክለውም ስርዓቱ የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ዋጋ በማስገኘትም ሀገሪቱ የያዘችውን ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚያግዝ ስርዓት በመሆኑ ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ሊተገብሩት ይገባል ያሉ ሲሆን በትግበራ ሂደት ለሚፈጠር ችግር ድጋፍ እንዲሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በበኩላቸው የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ  የግዢ ሥርዓት ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመቅረፍና ቀልጣፋ የግዢ ስርዓት በማስፈን ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው ያሉ ሲሆን ስርዓቱ በክልሉ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ የአስፈጻሚ፣ የሕግ አውጪ እና የተቆጣጣሪ ተቋማት  አመራሮች ተሳትፈዋል።

Validation workshop was held on Procurement and Property Administration Performance Audit Manual

 (April 23/2026), The Federal Government Procurement and Property Authority is an organization that has set a vision to become one of the leading institutions in Africa by 2030 by strengthening a modern public procurement and Property system. One of the activities it has undertaken to realize this vision is to improve, develop and implement legal and procedural systems.

One of the activities and responsibility of the authority strengthening audit and monitoring activities, so it has prepared an audit manual that can be implemented, and a validation workshop was held on the Procurement and Property Management Performance Audit Manual which was prepared. This workshop was held before implementation and will provide stakeholders with an opportunity to share their input on the manual.

In the workshop higher officials and other stakeholders was attended.

ባለስልጣኑ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምገባ መርሐግብር አከናወነ።

(ሚያዝያ 04/2018)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል በመገኘት ከ200 በላይ ለሚሆኑ ለአቅመ ደካማ የማሕበረሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራት የትንሳኤን በዓልን በጋራ አክብረዋል።

በምገባ መርሃግብሩ ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት በዓሉን ስናከብር የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንና አቅመ ደካሞችን በማሰብ መሆን እንዳለበት ገልጸው በተለይም እንዲህ አይነት ቦታዎች ላይ በመገኘት ፍቅርንና አንድነትን ማጋራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳየበት እንደመሆኑ ዕለቱን ተደጋግፎና ተረዳድቶ በማሳለፍ የክርስቶስን ዓላማ ማሳየት እንደሚገባ ያስገነዘቡ ሲሆን እንዲህ አይነት ሰው ተኮር ተግባራት ወደፊትም ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

(መጋቢት 24/218)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግሥት ግዥ አፈጻጸም እና ንብረት አስተዳደር ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት የሚወሰዱ አስተዳደራዊ ቅጣቶች አፈፃፀም  ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከግዥና ንብረት ሀላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ መመሪያው የተጠያቂነት መላላትን ለማስቀረት፣ ጠንካራ የህግና የአሰራር ስርዓትን ለመፍጠር እና ብልሹ አሰራርን እንዲወገድ ለማስቻል የተዘጋጀ ሲሆን  በረቂቅ መመሪያው ላይ ግልፅ ውይይትና ግንዛቤ መፍጠር በማስፈለጉ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የውይይት መነሻ ጽሁፉን ያቀረቡት በገንዘብ ሚኒስቴር የህግ መመሪያ ሀላፊ አቶ ተወዳጅ መሀመድ በበኩላቸው ይህ መመሪያ እንዲወጣ አስቀድሞ በአዋጅ 1333/2016 የተቀመጠ ሲሆን መመሪያው በየደረጃው ያሉ ከግዥና ንብረት ጋር የተገናኙ ሀላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሀላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ብሎም የግዥ አፈጻጸምና ንብረት አስተዳደር ስራው በሀላፊነት እንዲሰራ ለማስቻል የተዘጋጄ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ረቂቅ መመሪያው በማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት የተሾመ ወይም የተመደበ ሰው ከግዥ አፈፃፀም እና ንብረት አስተዳደር ጋር በተገናኘ ዓመታዊ የግዥ ዕቅድን፣ የግዥ አፈጻጸም ሪፖርቶችን፣ የንብረት አስተዳደር ሪፖርት በተገቢው የጥራት ደረጃና ግዜ ካላቀረበ እንዲሁም ጥቅም ላይ የማይውሉ እና አገልግሎታቸውን የጨረሱ ንብረቶችን በወቅቱ አለማስወገድ ወይም እንዲወገዱ አለማድረግ እና ሌሌችንም ዝርዝር ጥፋቶችን አካቷል፡፡

ረቂቅ መመሪያው የተዘረዘሩትን ጥፋቶችን ፈፅሞ የተገኘ የስራ ኃላፊና ተሿሚ እንደጥፋት ደረጃውና ድግግሞሹ የተለያዩ ማስጠንቀቂያና የገንዘብ መቀጫ እንደሚጣልበት ያብራራል፡፡

በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በክብርት ዋና ዳይሬክተሯ እና በሚመለከታቸው የባለስልጣኑ የስራ ሀላፊዎች ምላሽና መብራሪያ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡