Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

General

ባለስልጣኑ በተቋሙ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

(መጋቢት 20/ 2018)፣ የኢፌዴራ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከ2016-2018 መካከለኛ ዘመን እቅድ መጠናቀቁን ተከትሎ ከአስር ዓመቱ ስትራቴጂ እቅድ የተቀዳ አዲስ የመካከለኛ ዘመን (2019-2022) እቅድ አዘጋጅቷል።

ባለስልጣኑ ሰነዱን በማኔጅመንት ገምግሞ ሲያዳብር ቆይቶ ዛሬ ከባለስልጣኑ ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት ያለፈው የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ውጤታማ ነበር። ስለሆነም ከባለፈ የእቅድ አፈፃፀም በመነሳት ለበለጠ ስኬት መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።

 ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው በተለይም ይህ እቅድ የ10 ዓመቱ ስትራቴጂ እቅድ የመጨረሻው በመሆኑ ለስትራቴጂክ እቅዱ ስኬት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ያመላከቱ ሲሆን እቅዱን በትልቅ የአዕምሮ ዝግጁነትና ስነ ምግባር መፈጸም እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት በቀጣይ ዓመታት በተለይም ዲጂታል የግዥና ንብረት ስርዓትን ማጠናከር፣ የአልግሎት አሰጣጥ ግልጸኝነትን ማስፈን፣ የባለድርሻ አካላትን ትስስር ማጠናከር፣ የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግስት ግዥና ንብረት ማሻሻያ እና አቅም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ ሲሆኑ ባለፉት ሦስት ዓመታት (2016-2018)  በርካታ የአሰራር ሥርዓቶች እንደተዘረጉ፣ ዲጂታል አገልግሎትን ለማስፋት ሰፋፊ ስራዎች እንደተከናወነ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸዉንና የተገልጋይ እርካታን የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን ብሎም ሰፋፊ የሪፎርም ስራዎች መከናዎናቸውንና በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን አመልክቷል ።

አቶ መላኩ አዲሱን የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ (2019-2022) ዋና ዓላማ ባለስልጣኑ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን በማጠናከር ከአፍሪካ ቀዳሚ የመንግስት ግዥና ንብረት ተቆጣጣሪ ሆኖ የመገኘት ራዕይን እውን ማድረግ ሲሆን ዲጂታላዜሽንን ማጠናከር፣ ተቋማዊ አቅምን ማጎልበት፣ ዘላቂ ግዥና ንብረት ስርዓትን ማጠናከር፣ የመረጃና አገልግሎት ጥራትን ማሳደግ፣ የፖሊሲ፣ ማማከርና የምርምር ስራን ማጠናከር፣ ስትራቴጂካዊ ትብብርን ማጠናከር፣ የይግባኝን ጥፋተኝነት ስርዓትን ማጠናከር እንዲሁም የኦዲትና ክትትል ስራን ማጠናከር የሚሉ ዝርዝር ዓላማዎች እንዳካተተ አብራርተዋል።

አቶ መላኩ በማጠቃለያ ንግግራቸው የባለስልጣኑ ስኬት የሚለካው በእቅድ ብቻ ባለመሆኑ ለእቅዱ ስኬት ሁሉም በተሰጠው ሀላፊነት ልክ በትጋትና በቅንነት ሃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ከሰራተኞች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በክብርት ዋና ዳይሬክተሯ እና በሚመለከታቸው ስራ አስፈፃሚዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል። ምላሽና ማብራሪያውን ተከትሎ የቀሪ ወራት የስራ አቅጣጫ በክብርት ዋና ዳይሬክተሯ ክብርት ወ/ሮ መሰረት የቀጣይ ወራት የስራ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን በተለይም ከኦዲትና ቁጥጥር፣ ከዲጂታል አገልግሎት እንዲሁም ከአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።

ባለስልጣኑ የግዥ ኦዲትን እና የቁልፍ የግዥ አመላካቾችን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ በትጋት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት የግዥ ኦዲትን እና የቁልፍ የግዥ አመላካቾችን በሚመለከት ከክልል የግዥና ንብረት እንዲሁም ከፋይናንስ ሀላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂድዷል፡፡

የግዥ ኦዲትን በሚመለከት የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለልስጣን የመንግስት ግዥና ንብረት ክዋኔና ህጋዊነት ኦዲትና ክትትል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስ ጎዳና ሲሆኑ ኦዲት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ዋጋ እንዲያስገኝ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት መንገድ እንደሆነና በጥብቅ ስነ፟ ምግባር መከናወን እንዳለበት አብራርተዋል፡፡

አቶ አዲስ በገለጻቸው የኦዲት ዋና ዓላማ ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን ማሳደግ፣ ሕገወጥነትን፣ ማጭበርበርን እና ሙስናን መከላከል፣ ህጎችን እና መመሪያዎችን መከበራቸውን ማረጋገጥ፣ የውስጥ ቁጥጥርን ማጠናከርና የስጋት ከባቢን መቀነስ እንዲሁም ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ማስቻልና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ ሲሉ አክለዋል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኦዲት ስራ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው ያሉት አቶ አዲስ ማንኛውም የኦዲት ባለሙያ የኦዲትን መርህ ተከትሎ ማከናወንም እንዳለብት አመላክተዋል፡፡ እንደ አቶ አዲስ ገለጻ አንድ ኦዲተር ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ተጠያቂነትን የተላበሰ፣ ታማኝነት እና ምስጉን ስነ ምግባር ያለው እና የኦዲት መርሆን መከተል ይኖርበታል ብለዋል፡፡

አቶ አዲስ በማጠቃለያ ገለጻቸው በ2017 በጀት ዓመት የታዩ የኦዲት ግኝቶችን ለተወያዮች ያቀረቡ ሲሆን የቀጣይ የእርምት አቅጣጫዎችንም ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱ ከግዥ ኦዲት በተጨማሪ በቁልፍ የግዥ አመላካቾች ላይ በአቶ እሸቱ አጥናፉ እና በአቶ ጸጋዬ አበበ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ምላሽና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

የሀገራችንን ልማት ለማፋጠን እና ለዜጎቻችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነትና በትብብር መስራት ይኖርብናል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ

(መጋቢት 16/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ  ከክልል የግዥና ንብረት እንዲሁም ከፋይናንስ ሀላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር እያካሄደ ይገኛል። በምክክር መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት የመንግስታዊ አገልግሎት ዋና መሠረቶች የግልጽነት፣ የተጠያቂነት፣ የቅልጥፍና እና የተገቢ የገንዘብ አጠቃቀም ሲሆኑ ይህንን ለማሳካት ደግሞ ዲጂታል ስርዓቶችን መጠቀም አስፈላጊ እንደተገኘ ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት (e-GP sytem) የግዥ ሂደቶችን በማቀላጠፍ፣ የሰው ጣልቃ ገብነትን በመቀነስ እና የመረጃ ግልጽነትን በማሳደግ የሀገር ሀብት እንዲጠበቅ ይረዳል ሲሉ አብራርተዋል። በተጨማሪም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሽከርካሪ ስምሪትና አስተዳደርና ነዳጅ አጠቃቀም ስርዓትን (e-fleet management system) እና ሌሎችንም የአሰራር ስር ዓቶች ዘርግቶ በውጤታማነት እየሰራባቸው ይገኛል ሲሉ አመላክተዋል።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ስኬት በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ያለው አገልግሎት እና ተሳትፎ ላይ የሚመሰረት በመሆኑ ተቋማትን በአቅም ማጎልበት፣ ባለሙያዎችን ማብቃት፣ ቴክኖሎጂን ማስፋፋት እና የህግ አፈጻጸምን ማጠናከር የሁላችንም ትኩረት መሆኑ ይኖርበታል ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ አፈጻጸምን በገለጹበት ንግግራቸው ወደ ክልሎች እየወረደ እንደሆነና በተለይም በአዲ አበባ ከተማ መስተዳደር  ከፓይለት 13 ተቋማት በተጨማሪ 55 ተቋማት ስር ዓቱን እየተገበሩ መሆናቸው፣ በኦሮሚያ ክልል በ16 ተቋማት መተግበር መቻሉ፣ ሌሎች 7 ክልሎች ስር ዓቱን ለመተግበር በመሰረተ ልማትና በቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸው እንዲሁም ደቡብ  ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሶማሌ፣ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለመጀመር የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደተሰጣችውና ሌሎችንም ክልሎች ለማስገባት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህግ ማዕቀፎችን ከመተግበር አንጻርም የግዥና ንብረት አዋጅ 1333/2016 ስራ ላይ ከመዋሉ ጋር ተያይዞ ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮችም ከፌደራሉ ጋር የተጣጣመ የአዋጅ እና መመሪያ ዝግጅት እንዳደረጉና አብዛኛዎቹ እንዳጸደቁ ገለጸዋል።

ክብርት ወ/ሮ መሰረት በማጠቃለያ ንግግራቸው ሁላችንም የሀገራችንን ልማት ለማፋጠን እና ለዜጎቻችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት፣ በትብብር እና በአመራር ኃይል መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የግዥና ንብረት ማሻሻያና አቅም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አገልግሎቱን በውጤታማነት ለመምራት የህግ ማዕቀፎችን ከማሻሻል ጀምሮ ሰፋፊ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝና ክልሎችም የህግ ማዕቀፎቻቸውን ከፌዴራሉ የግዥና ንብረት የህግ ማዕቀፎች ጋር ተቀራራቢ እንዲሆን ለማድረግ ተከታታይ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ እና አብዛኞቹ ክልሎችም የህግ ማዕቀፎቻቸውን ከፌዴራሉ የግዥና ንብረት ህጎች ጋር የማጣጣም ስራ እንደሰሩ አመላክተዋል።

በሌላ በኩል የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትን (e- GP System) ወደ ክልሎች ማወረድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ገለጻ ያደረጉት የፒራጎ መስራችና ማናጀር አቶ እውነቱ አበራ እንደገለጹት ስርዓቱን ወደ ክልሎች ለማውረድ የመንግስት ግዥና ንብረትም ይሁን ፒራጉ ዝግጁ እንደሆኑ ይልቁንም ክልሎች አስቀድመው ስምምነት መፈራረም፣ ፕሮጀክቱን የሚመራና ሀላፊነት የሚወስድ ባለሙያ መመድብ፣ የስልጠና ማዕከላትን ማሟላትና መሰል ጉዳዮችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው አብራርተዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የእለቱ የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

While there are many countries supported by World Bank to implement digital procurement systems, only Ethiopian e-GP System has been successfully implement it.

(March 24/2026), Federal Government Procurement and Property Authority held a discussion with the World Bank Procurement Manager Eastern and Southern Africa Region, Mrs. Elmas Arisory, and their partners on a ways to increase the effectiveness of the electronic government procurement system.

The Director General of the Authority, H.E. Mrs. Meseret Meskele, who presented the opening speech for the discussion, explained that the Authority has carried out extensive transformational work in the past three years and is achieving the desired results in the transformational work.

In her statement, the H.E. Mrs. Meserete indicated that the authority has made significant changes in recent years, starting from amending the Procurement and property Proclamation. And also plays crucial role in the implementation of procurement directive, property directive and other operational systems, in order to modernize procurement and property system and become the first institution in Africa. She explained that the authority is also fully implementing its service delivery, especially e-learning, Letter management, compliant handling system, case management system, corruption report, free call service, reporting system for misconduct and similar services are fully digitalize.

Despite this, she explained that there were problems in maintaining the electronic government procurement system and that the authority was competent to do so. In particular, capacity limitations, supplier readiness, lack of bench marking, lack of infrastructure were the main issues that hindered the system. In her presentation, H.E. Mrs. Meseret indicated the prior areas of the Authority in the coming years; including increasing institutional capacity, continuing the transformation work effectively, insuring sustainable public procurement, Improving Service and data quality, Professionalization training and implementing digital 2030.

On the other hand, the World Bank Procurement Manager Eastern and Southern Africa Region, Mrs. Elmas Arisory, said that although the Bank has been assisting many countries to implement digital procurement systems, only the Ethiopian electronic government procurement is continuing effectively. Mrs. Elmas Arisory expressed her happiness that the project has continued successfully and assured that they will continue to provide financial and technical support to ensure the effectiveness of project.

She added that Out of more than 200 countries in the world that implement electronic procurement, Ethiopia is the only one that has met the World Bank’s requirements for implementing, and gave green light for all Bank Procurements should be implemented through e- GP system.

Mrs. Elmas Arisory concluded that the project must continue effectively and the Bank is ready to provide the expected supports. What is expected from the authority should be provided with the necessary support and the time required from the bank.