Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለሥልጣኑ በ13ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር የአራተኛ ደረጃ የጥራት ዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበረከተለት፡፡

(ኅዳር 12/2019 ዓ.ም.|አዲስ አበባ)  የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት (EQA) ባዘጋጀው 13ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር የፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአራተኛ ደረጃ የጥራት ዕውቅና ሰርቲፊኬት (Fourth Level Quality Recognition Certificate) አሸናፊ በመሆን ተሸለመ።

ዕውቅናው በኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ቴዎድሮስ መብራት እና በድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ በዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ የኢፌዴሪ ፕሬዘደንት ክቡር አቶ ታዬ አጽቀስላሴ እና ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተምስገን ጥሩነህ በተገኙበት ለባለሥልጣኑ ተበርክቷል።

ባለሥልጣኑ ይህንን ከፍተኛ ደረጃ ዕውቅና ሊያገኝ የቻለው የተቋሙን የአሠራር ጥራት፣ ግልጽነትና ቅልጥፍና ለማሳደግ በተከታታይ ሲያከናውን የቆየውን ዘርፈ ብዙ የሪፎርምና የአቅም ግንባታ ሥራ መሠረት በማድረግ ነው። በተለይም ሕዝብና ባለድርሻ አካላት የሚተማመኑበት፣ ተጠያቂነት የሰፈነበትና ዘመናዊ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ተቋም ሆኖ ለመገኘት የተወሰዱ እርምጃዎች ብሎም ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፈትኛ ዋጋ እንዲያስገኝ ለማድረግ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች ለውጤቱ መገኘት ወሳኝ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በሂደቱም ከሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ ዝግጅትና ማሻሻያ ጀምሮ እስከ ዕለት ተዕለት የአሠራር አፈጻጸምና የአገልግሎት አሰጣጥ ድረስ አመርቂና ተጨባጭ ለውጥ ያመጡ ሥራዎች ተከናውነዋል። የአሠራር ሥርዓቶችን ማዘመን፣ የሕግ ማዕቀፎችን ከወቅታዊ ፍላጎት ጋር ማጣጣም እና በጥራት ላይ የተመሠረተ ተቋማዊ ባህልን ማስረጽ ባለሥልጣኑ በገለልተኛ ገምጋሚዎች ሲመዘን ከፍተኛ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።

ይህ የአራተኛ ደረጃ የጥራት ዕውቅና ሰርቲፊኬት ባለሥልጣኑ የጀመረውን የጥራትና የቅልጥፍና ጉዞ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ወደፊትም የመንግሥት ግዥና ንብረት ሥርዓትን ይበልጥ በማጠናከር ለብሔራዊ ልማትና ለመልካም አስተዳደር ሰፊ ዕገዛ ለማድረግ ተጨማሪ አቅምና ኃላፊነት የሚፈጥር ይሆናል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *