ባለስልጣኑ የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን ገመገመ፡፡

(ታህሳሰ 25/2018 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በጋራ ገምገመዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ዲጅታላይዜሽን፣ ከዘለቄታዊነት የግዥና /Sustainable Procurement/ ንብረት አስተዳደር ሥርዓት ማጎልበት፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት አገልግሎት እና መረጃ ጥራትና ሽፋን ማሳደግ፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት የፖሊሲ፣ ማማከር አገልግሎት እና የጥናትና የምርምር፣ ከመፈፀምና ማስፈፀም አቅም ግንባታ፣ ሙያዊ ድጋፍ፣ ክትትል የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ከመስጠት፣ ከስትራቴጂያዊ የቴክኒክ ትብብር እና አጋርነትን ከማጠናከር፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ኦዲትና ክትትል ሥራዎችን ጥራትና ሽፋን ከማሳደግ እንዲሁም ከግዥ አፈፃፀም እና ንብረት ሽያጭ ላይ የሚቀርቡ የይግባኝና የጥፋተኝነት ውሳኔ አሰጣጥን ከማጠናከር አንጻር የተቋሙን አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
ባለስልጣኑ የአሰራር ስርዓቱን ጥራትና ቅልጥፍና ለማሳደግ አዋጁን ጨምሮ መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1073/2017፣ የንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1095/2017፣ የተሸከርካሪ ስምሪት፣ ነዳጅ አጠቃቀም ሥርዓት (Fleet Management System) እና ሌሎች አሰራር ስርዓቶች ላይ ለተገልጋዮች እና ለባለድርሻ አካላት ተከታታይ ሥልጠና መስጠቱን በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
ተቋሙ በትኩረት እየተገበራቸው ከሚገኙ አበይት ተግባራት አንዱ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) ወደ ክልሎች ማውረድ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ቀድመው የጀመሩትን አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና ኦሮሚያ ክልልን ከመደገፍ በተጨማሪ በግማሽ ዓመቱ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለሶማሌ ክልል፣ ለአማራ ክልል እና ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ስርዓቱን ሊተገብሩ በሚችሉብት ሁኔታ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ መሰጠቱም ተብራርቷል፡፡
ሌላው ተቋሙ በትኩረት ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት አንዱ የኦዲት ስራ ሲሆን በግማሽ ዓመት በ34 ተቋማት ላይ የህጋዊነት ኦዲት፡ በ26 ተቋማት ላይ የክትትል ስራ፣ በ6 ተቋማት ላይ የጥቆማ ኦዲት እንደተሰራ በሪፖርቱ ተካትቷል፡፡ ይህም አፈጻጸሙን ስንመለከት በቅደም ተከተል 85%፣ 104%፣ 100% ሆኖ መጠናቀቁን ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ይግባኝና ጥፋተኝነትን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ 70 ጉዳዮች መረጃ ተሟልቶላቸው ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቀረቡ ሲሆን ሁሉም ውሳኔ እንደተሰጠባቸው የተብራራ ሲሆን የጥፋተኝነት ሪፖርቶችን በሚመለከት 75 ሪፖርቶች መረጃ ተሟልቶላቸው ቀርበው 69 የጥፋተኝነት ሪፖርቶች ውሳኔ እንዲያገኙ ይህም 92% አፈጻጸም እንዳለው ተብራርቷል፡፡
በመጨረሻም የሪፎርም ስራዎችን አጠንክሮ ማስቀጠል፣ የድጋፍና ስልጠና ስራዎችን ማጠናከር፣ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን ወደ ክልሎች ለማውረድ ተጨማሪ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ በዋና ዳይሬክተሯ ክብርት ወ/ሮ መሰረት አቅጣጫ ተቀምጦ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

















0 Comments