Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ ከክልል ግዥና ንብረት ተቆጣጣሪ አካላት፣ ከመንገድ ሴክተር የክልል ቢሮ ሀላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት አካሄደ።

(መስከረም 29/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የግዥ ጥራትና ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት ከክልል ግዥና ንብረት ተቆጣጣሪ አካላት እና ከመንገድ ሴክተር የክልል ቢሮ ሀላፊዎች ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት ውይይቱ ቁልፍ የግዥ አመላካቾች እና የግዥ ኦዲት ላይ ተወያይቶ የጋራ መግባባት መድረስ መሆኑን አመላክተዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው የገጠር መንገድና መሰረተ ልማት ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ እና የሚዘረጋው የገጠር መንገድና መሰረተ ልማት ጥራትና ታማኝነትን ያማከሉ እንዲሆኑ ከቁልፍ የግዥ ሂደቶች በተጨማሪ ኦዲት መደረግ ያለበት በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨባጫ መድረኩ እንደተዘጋጄ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል የመጀመሪያውን ገላጻ ያቀረቡት  በከተማና መሰረት ልማት ሚኒስቴር የገጠር ልማትና ትሥስር ፕሮግራም ማናጀር አቶ መሃመድ አሚን ሲሆኑ በዋናነት የገጠር መሰረተ ልማት የማህበረሰብን ተሥስር በመፈጠር፣ የንግድ ትሥስርን በመፍጠር፣ ጤና ጣቢያዎች እና ትምህርት ቤቶች ከማህበረሰቡ እንዲገናኙ በማድረግ በኩል የጎላ ሚና ያለውና ከፍተኛ በጀት የሚበጀትለት በመሆኑ በህግ መመራት ብሎም የኦዲት ክትትል መደረግ ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ የክልል አመራሮች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ውይይቶችን ማድረግና በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብልዋል።

በቁል የግዥ መለኪያዎች ላይ ገለጻ ያቀረቡት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከፍተኛ የፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጸጋዬ አበበ በበኩላቸው ቁልፍ የግዥ መለኪያዎች የግዥ መርሆቻችን በትክክል መተግበራቸውን የምናይበትና የምንለካበት መከታተያ መሳሪያ በመሆኑ የሚፈጸመው ግዥ ቁልፍ የግዥ መለኪያዎችን ያሟላ መሆን ይኖርብታል ሲሉ አብራርተዋል።

በእልቱ የግዥ ኦዲትን በሚመለከት በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የክዋኔና የህጋዊነት ኦዲት ክትትል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስ ጎዳና ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። አቶ አዲስ በገለጻቸው ኦዲተሮች የተቋም መሪዎች አጋዥ በመሆናቸው መሪዎች ሊደግፏቸውና በመርህ እንዲመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

ገለጻዎችን ተከትሎ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *