Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

ባለስልጣኑ ለከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርከፍተኛ እና መካከለኛ አመራርበግዥ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡

(ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም)፣ የግዥና ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራትና ቅልጥፍና ለመጨመር ብሎም ዲጂታል አሰራርን የተቋሙ ባህል ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ባለስልጣኑ በተለይም የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ አዋጅ ቁጥር 1333/2016 እና አውጁን ለማስፈጸም የወጡ መመሪያዎችን በጥብቅ ዲስፒሊን እንዲተገበሩ ለተቋማት ስልጠናዎችን እየሰጠነ እና እየደገፈ ይገኛል፡፡ በዚህም ለከተማና መሰረተ ልማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራር በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1073/2017 ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኔ ሲሆኑ የግዥ ሂደታችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅ እንዲሁም አዋጁን ለማስፈጸም የወጡ መመሪያዎችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህን በትክክል ለማወቅና ለመረዳት መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ከማንበብ በዘለለ በስልጠና ማዳበሩ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የግዥና ንብረት መምሪያዎች እና የአሰራር ስርዓቶች በሚዘጋጁበት ወቅት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች ላደረጉት የአመራርና የቴክኒክ ድጋፍ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት አመሰግነዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው የከተማ እና ልማት ሚኒስቴር ሰፊ ግዥ የሚፈጸምበትና ከፍተኛ የመንግስት በጀት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ የግዥና ንብረት አሰራርን አውቆ መተግበር በግዥ ሂደት ከሚከሰት ስህተት ለመውጣትና የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማሻሻያና አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ በስልጠናቸው ዋና ዋና የግዥ መርሆች፣ የልዩ ፈቃድ አሰጣጥና ሁኔታ፣ የግዥ ስልቶች፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የባለስልጣኑ እና የገዥው ተቋም ተግባርና ሀላፊነት እና ሌሎችን የመመሪያ ክፍሎች በገለጻቸው አካተዋል፡፡

አቶ መላኩ በተለይም የግዥና ንብረት ባለስልጣን ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ፣ የግዥና ንብረት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ አስፈላጊ የሆኑ የጨራታ ሰነዶችንና ማኑዋሎችን በማዘጋጀት፣ በፌዴራል እና በክልሎች መካከል የተጣጣመ የግዥና ንብረት ህጎች እንዲኖሩ በመስራት፣ የሚቀርቡ የጥፋተኝነት ሪፖርቶችን በማጣራት ውሳኔ በመስጠት እና የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትን በመቆጣጠር እና በማስተዳደር በኩል ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አቶ መላኩ አክለውም በመመሪያው የግዥ ልዩ አስተያየት የተካተተ ሲሆን የልዩ አስተያየት ዋና አላማም አምራች ኢንዱስትሪውን ማበረታታት፣ መንግስት የጀመረውን ሪፎርም እውን ማድረግ እና የሀገር ውስጥ ምርት ተጠቃሚነት ባህልን ማበረታታት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በክብርት ዋና ዳይሬክተሯ እና በአቶ መላኩ ተጓዴ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *