Skip to contentSkip to main navigation Skip to footer

News

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራር ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

(ጥር 02/2018 ዓ.ም)፣ የመንግስት ግዥን ንብረት ባለስልጣን ከኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢዎች፣ ከፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከአማካሪ ኮሚቴ አመራር እና ከምክር ቤቱ ሴቶች ኮከስ አመራሮች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ውይይቱ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን እያከናወናቸው በሚገኙ ክንውኖች፣ የዲጂታል ስራዎች፣ የግዥና ንብረት የህግ ማዕቀፎች እና ወደፊት በትኩረት ሊሰራባቸው በታቀዱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በ2019 በጀት አመት የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) ሙሉ በሙሉ ይተገብራል። አቶ አባተ ምትኩ

(ጥር 01/2018 ዓ.ም)፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓቱን አዘምኖ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ስራዎችን ዲጂታላይዝ የማድረግ እየሰራ ይገኛል። በዚህ ረገድ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) ተጠቃሽ ሲሆን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርምን በመደገፍ በኩል ያለው ፋይዳም የጎላ ነው።

ባለስልጣኑ በአሁኑ ወቅት ሁሉን የፌዴራል ተቋማትና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቻቸው ግዣቸውን ሙሉ በሙሉ በመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP) እንዲፈጽሙ ያስቻለ እና ወደ ክልሎችም ስርዓቱን እያስተገበረ የሚገኝ ሲሆን የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስርዓቱን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሩ እንዲሁም ለግዥና ንብረት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የስልጠናውን አስፈላጊነትና ቀጣይ ሂደትን በማስመከት ገለጻ ያደረኩት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ሲሆኑ ስርዓቱ ለትግበራ ምቹ፣ ውጢታማነትን የሚያረጋግጥ፣ ጊዜን የሚቆጥብና ታማኝነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አብራርተዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስርዓቱን ጀምሮ ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ በኩል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ድጋፉ እንደማይለየው ገለጸዋል።

በሌላ በኩል የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በ2019 በጀት አመት የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) ሙሉ በሙሉ መተግበር እንደሚገባ  ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባተ ምትኩ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት ምንም እንኳ ተቋሙ ከመንግስት ተቋማት የተለዬ ባህሪ ቢኖረውም ስርዓቱ ሊያሰራ የሚችልና አንዳንድ ጉዳዮችን ተቀራርበን በመስራት የምንፈታቸው በመሆናቸው ስርዓቱን ያለማቅማማት በፍጥነት መጀመር ይኖርብናል ብለዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በተለይም አዋጅ ቁጥር 1333/2016 እና አዋጁን ለማስፈጽም የወጡ መመሪያዎች ላይ የተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች እና የህግ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት በአቶ መላኩ ተጓዴ የተብራራ ሲሆን የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትን በሚመለከት ደግሞ በአቶ ያፌት መኮንን ገለጻ ቀርቧል።

ከገለጻው በኋላ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች ቀርበው በባለስልጣኑ አመራር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ባለስልጣኑ የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን ገመገመ፡፡

(ታህሳሰ 25/2018 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በጋራ ገምገመዋል፡፡

ባለስልጣኑ ከተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ዲጅታላይዜሽን፣ ከዘለቄታዊነት የግዥና /Sustainable Procurement/ ንብረት አስተዳደር ሥርዓት ማጎልበት፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት አገልግሎት እና መረጃ ጥራትና ሽፋን ማሳደግ፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት የፖሊሲ፣ ማማከር አገልግሎት እና የጥናትና የምርምር፣ ከመፈፀምና ማስፈፀም አቅም ግንባታ፣ ሙያዊ ድጋፍ፣ ክትትል የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ከመስጠት፣ ከስትራቴጂያዊ የቴክኒክ ትብብር እና አጋርነትን ከማጠናከር፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ኦዲትና ክትትል ሥራዎችን ጥራትና ሽፋን ከማሳደግ እንዲሁም ከግዥ አፈፃፀም እና ንብረት ሽያጭ ላይ የሚቀርቡ የይግባኝና የጥፋተኝነት ውሳኔ አሰጣጥን ከማጠናከር አንጻር የተቋሙን አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

ባለስልጣኑ የአሰራር ስርዓቱን ጥራትና ቅልጥፍና ለማሳደግ አዋጁን ጨምሮ መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1073/2017፣ የንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1095/2017፣ የተሸከርካሪ ስምሪት፣ ነዳጅ አጠቃቀም ሥርዓት (Fleet Management System) እና ሌሎች አሰራር ስርዓቶች ላይ ለተገልጋዮች እና ለባለድርሻ አካላት ተከታታይ ሥልጠና መስጠቱን በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ በትኩረት እየተገበራቸው ከሚገኙ አበይት ተግባራት አንዱ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) ወደ ክልሎች ማውረድ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ቀድመው የጀመሩትን አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና ኦሮሚያ ክልልን ከመደገፍ በተጨማሪ በግማሽ ዓመቱ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለሶማሌ ክልል፣ ለአማራ ክልል እና ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ስርዓቱን ሊተገብሩ በሚችሉብት ሁኔታ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ መሰጠቱም ተብራርቷል፡፡

ሌላው ተቋሙ በትኩረት ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት አንዱ የኦዲት ስራ ሲሆን በግማሽ ዓመት  በ34 ተቋማት ላይ የህጋዊነት ኦዲት፡ በ26 ተቋማት ላይ የክትትል ስራ፣ በ6 ተቋማት ላይ የጥቆማ ኦዲት እንደተሰራ በሪፖርቱ ተካትቷል፡፡ ይህም አፈጻጸሙን ስንመለከት በቅደም ተከተል 85%፣ 104%፣ 100% ሆኖ መጠናቀቁን ሪፖርቱ ያመላክታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ይግባኝና ጥፋተኝነትን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ 70 ጉዳዮች መረጃ ተሟልቶላቸው ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቀረቡ ሲሆን ሁሉም ውሳኔ እንደተሰጠባቸው የተብራራ ሲሆን የጥፋተኝነት ሪፖርቶችን በሚመለከት 75 ሪፖርቶች መረጃ ተሟልቶላቸው ቀርበው 69 የጥፋተኝነት ሪፖርቶች ውሳኔ እንዲያገኙ ይህም 92% አፈጻጸም እንዳለው ተብራርቷል፡፡

በመጨረሻም የሪፎርም ስራዎችን አጠንክሮ ማስቀጠል፣ የድጋፍና ስልጠና ስራዎችን ማጠናከር፣ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን ወደ ክልሎች ለማውረድ ተጨማሪ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ በዋና ዳይሬክተሯ ክብርት ወ/ሮ መሰረት አቅጣጫ ተቀምጦ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

ባለስልጣኑ ለከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርከፍተኛ እና መካከለኛ አመራርበግዥ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡

(ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም)፣ የግዥና ንብረት ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራትና ቅልጥፍና ለመጨመር ብሎም ዲጂታል አሰራርን የተቋሙ ባህል ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ባለስልጣኑ በተለይም የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ አዋጅ ቁጥር 1333/2016 እና አውጁን ለማስፈጸም የወጡ መመሪያዎችን በጥብቅ ዲስፒሊን እንዲተገበሩ ለተቋማት ስልጠናዎችን እየሰጠነ እና እየደገፈ ይገኛል፡፡ በዚህም ለከተማና መሰረተ ልማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራር በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1073/2017 ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኔ ሲሆኑ የግዥ ሂደታችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅ እንዲሁም አዋጁን ለማስፈጸም የወጡ መመሪያዎችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህን በትክክል ለማወቅና ለመረዳት መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ከማንበብ በዘለለ በስልጠና ማዳበሩ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የግዥና ንብረት መምሪያዎች እና የአሰራር ስርዓቶች በሚዘጋጁበት ወቅት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች ላደረጉት የአመራርና የቴክኒክ ድጋፍ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት አመሰግነዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው የከተማ እና ልማት ሚኒስቴር ሰፊ ግዥ የሚፈጸምበትና ከፍተኛ የመንግስት በጀት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ የግዥና ንብረት አሰራርን አውቆ መተግበር በግዥ ሂደት ከሚከሰት ስህተት ለመውጣትና የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማሻሻያና አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ በስልጠናቸው ዋና ዋና የግዥ መርሆች፣ የልዩ ፈቃድ አሰጣጥና ሁኔታ፣ የግዥ ስልቶች፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የባለስልጣኑ እና የገዥው ተቋም ተግባርና ሀላፊነት እና ሌሎችን የመመሪያ ክፍሎች በገለጻቸው አካተዋል፡፡

አቶ መላኩ በተለይም የግዥና ንብረት ባለስልጣን ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ፣ የግዥና ንብረት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ አስፈላጊ የሆኑ የጨራታ ሰነዶችንና ማኑዋሎችን በማዘጋጀት፣ በፌዴራል እና በክልሎች መካከል የተጣጣመ የግዥና ንብረት ህጎች እንዲኖሩ በመስራት፣ የሚቀርቡ የጥፋተኝነት ሪፖርቶችን በማጣራት ውሳኔ በመስጠት እና የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትን በመቆጣጠር እና በማስተዳደር በኩል ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አቶ መላኩ አክለውም በመመሪያው የግዥ ልዩ አስተያየት የተካተተ ሲሆን የልዩ አስተያየት ዋና አላማም አምራች ኢንዱስትሪውን ማበረታታት፣ መንግስት የጀመረውን ሪፎርም እውን ማድረግ እና የሀገር ውስጥ ምርት ተጠቃሚነት ባህልን ማበረታታት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በክብርት ዋና ዳይሬክተሯ እና በአቶ መላኩ ተጓዴ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡