ከሁሉም ባንኮችና ኢንሹራንሶች ጋር በኢጂፒ ሲሰተም ትስስር ትግበራ ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ በመክፈቻ ንግግራቸዉ ባለስልጣኑ የዲጅታላይዜሽን እና የትራንስፎርሜሽን ጉዞን ከተቀላቀለ ጊዜ ጀምሮ አሰራርን ዘመናዊ፤ቀልጣፋና ዉጤታማ ለማድረግ በዘርፉ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ተቋም መሆኑን አስታዉሰዉ በተለይም የኢጂፒ ሲስተምን በመጠቀም ቀደም ሲል የተተገበሩና በቀጣይም የተሻሻሉ ትግበራዎችን ጭምር የሲስተሙ አካል በማድረግ ከመተግበር በዘለለ ለንግዱ ማህበረሰብ በኢጂፒ ሲስተም ዙሪያ በቂ መረጃ እንዲኖረዉ በአካል ከሚሰጠዉ ድጋፍ በተጨማሪ በበይነ-መረብ ለመስጠት የሚያሥችል ስርዓት ተጠናቅቆ ወደ ተግባር መገባቱን ጭምር ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡
አያይዘዉም ሲስተሙን ቀደም ሲል ከሌሎች ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ተግባር መከናወኑን ገልጸዉ የዚሁ መድረክ ዋነኛ ዓላማም ባንኮችንና ኢንሹራንሶችን ከመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ጋር ማስተሳሰር መሆኑን በመጠቆም በተለይም ከግዥ ጋር የተያያዙ ማስተግበሪያዎችን ሲስተሙን ተጠቅመዉ የንግዱ ማህበረሰብ (አቅራቢዎች) ደንበኛ ከሆኑበት የትኛዉም የባንክና የኢንሹራንስ አማራጮች በኦንላይን እንዲያዙ የሚስችላቸዉን የሲስተም ዝርጋታ ትዉዉቅ በማድረግ በይፋ ለማስጀመር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
READ MORE >>