Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ሰውን የማገዝ ምንጩ ሰው መሆን ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ

(ሀምሌ 23/2017 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በያዝነው የክረምት ወቅት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከአከናዎናቸው የበጎ አድራጎት ተግባራት አንዱ ማዕድ ማጋራት ሲሆን ዛሬ የባለስልጣኑን ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌን ጨምሮ ሁሉም አመራር በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በመገኘት ማህበሩ እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት፣ ከ1000 በላይ አረጋውያን ማዕድ የማጋራትና  የማበረታታት ስራ ስርቷል፡፡

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በመላ ሀገራችን 46 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በአጠቃላይ ከ8500 በላይ አረጋውያንን፣ አቅመ ደካሞችንና ህሙማንን ተቀብሎ የሚያኖር፣ የሚንከባክብ፣ የሚያሳክምና የሚጦር ማህበር መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም በማህብሩ ውስጥ ማህበራዊ እና ሀይማኖታዊ ትውፊቶች ሳይቀር እኩል የሚስተናገዱበት ሂደት ኢትዮጵያን በአንድ ጣራ ስር እንድናያት የሚያደርግ እንደሆነ ተገለጿል፡፡

በማዕድ ማጋራቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ  በንግግራቸው መንግስት ፖሊሲ ቀርጾ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በምገባ፣ በትምህርት ቁሳቁስ፣ የአረጋውያንን ቤት በማደስ እና በመሳሰሉት ድጋፍ ማድረግ መሆኑን የገለጹ ሲሆን  ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያደረገው ድጋፍም የዚህ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው ሰውን የመደገፍ ምንጩ ሰው መሆናችን በመሆኑ መቄዶንያን መደገፍ ሀገርን መደገፍ ነው ምክያቱም ኢትዮጵያን በትክክል ልናያትና ልናውቃት የምንችለው መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ውስጥ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ የክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የሆነ ማህበር ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ የክቡር ዶክተር ቢኒያም መቄዶንያ ምንም ሳይኖረው የተነሳ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ለምገባ በቀን ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ማህበር ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቅን የኢትዮጵያ ልቦች የሚከናወን ነው በለዋል፡፡ የክቡር ዶክተር ቢኒያም አያይዘውም መቄዶንያ አሁን ላይ የሆስፒታል እና የአረጋውያን መጠለያን ጨምሮ ተደራሽነቱን ማስፋትም አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ቢወጣ ስራዎችን ማቅለል እንችላለን ብለዋል፡፡

በእለቱ የግዥና ንብረት ባለስልጣን ባከናወነም መልካም ተግባር እለቱ በቋሚነት በባለስልጣኑ ስም እንዲታወስ በአረጋውያን የተጠየቀ ሲሆን ሀምሌ 23 በየአመቱ “የመልካምነት ቀን” ተብላ አረጋውያንን በመንከባከብና መልካም በማድረግ የምትታሰብ ይሆናል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *