የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የህብር ቀንን አከበር፡፡
ዻጉሜ 4/2016 የህብር ቀን የሚል ሰያሜ ተሰጥቶት በመላ ሀገሪቱ በተለያየ ሁነት መከበሩን ተከትሎ ነዉ ባለስልጣኑም የህብር ቀንን በአብሮነት ለማሳለፍና ለማክበር የወሰነዉ፡፡
በዓሉን መላዉ የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በስፍራዉ በመገኘት ያከበሩ ሲሆን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በቦታዉ ተገኝተዉ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክትና የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል፡፡
በመቀጠልም ወርሃዊ የደመወዝ መጠናቸዉ ከ3000 ብር በታች ለሆኑ የባለስልጣኑ ሰራተኞች በዚሁ በህብር ቀን ህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን ለማሳየት አብሮነትን ታሳቢ ያደረገ የዓይነት ድጋፍ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በመጨረሻም ለአብሮነታችን ማሳያ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀዉን ማዕድ በጋራ በመቋደስ የዓሮግራሙ ፈጻሜ ሆኗል፡፡ ቀደም ሲል ባለስልጣኑ የሪፎርም ቀንን ማክበሩ ይታወሳል፡፡
0 Comments