Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

News

ሰውን የማገዝ ምንጩ ሰው መሆን ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ

(ሀምሌ 23/2017 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በያዝነው የክረምት ወቅት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከአከናዎናቸው የበጎ አድራጎት ተግባራት አንዱ ማዕድ ማጋራት ሲሆን ዛሬ የባለስልጣኑን ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌን ጨምሮ ሁሉም አመራር በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በመገኘት ማህበሩ እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት፣ ከ1000 በላይ አረጋውያን ማዕድ የማጋራትና  የማበረታታት ስራ ስርቷል፡፡

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በመላ ሀገራችን 46 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በአጠቃላይ ከ8500 በላይ አረጋውያንን፣ አቅመ ደካሞችንና ህሙማንን ተቀብሎ የሚያኖር፣ የሚንከባክብ፣ የሚያሳክምና የሚጦር ማህበር መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም በማህብሩ ውስጥ ማህበራዊ እና ሀይማኖታዊ ትውፊቶች ሳይቀር እኩል የሚስተናገዱበት ሂደት ኢትዮጵያን በአንድ ጣራ ስር እንድናያት የሚያደርግ እንደሆነ ተገለጿል፡፡

በማዕድ ማጋራቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ  በንግግራቸው መንግስት ፖሊሲ ቀርጾ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በምገባ፣ በትምህርት ቁሳቁስ፣ የአረጋውያንን ቤት በማደስ እና በመሳሰሉት ድጋፍ ማድረግ መሆኑን የገለጹ ሲሆን  ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያደረገው ድጋፍም የዚህ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው ሰውን የመደገፍ ምንጩ ሰው መሆናችን በመሆኑ መቄዶንያን መደገፍ ሀገርን መደገፍ ነው ምክያቱም ኢትዮጵያን በትክክል ልናያትና ልናውቃት የምንችለው መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ውስጥ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ የክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የሆነ ማህበር ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ የክቡር ዶክተር ቢኒያም መቄዶንያ ምንም ሳይኖረው የተነሳ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ለምገባ በቀን ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ማህበር ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቅን የኢትዮጵያ ልቦች የሚከናወን ነው በለዋል፡፡ የክቡር ዶክተር ቢኒያም አያይዘውም መቄዶንያ አሁን ላይ የሆስፒታል እና የአረጋውያን መጠለያን ጨምሮ ተደራሽነቱን ማስፋትም አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ቢወጣ ስራዎችን ማቅለል እንችላለን ብለዋል፡፡

በእለቱ የግዥና ንብረት ባለስልጣን ባከናወነም መልካም ተግባር እለቱ በቋሚነት በባለስልጣኑ ስም እንዲታወስ በአረጋውያን የተጠየቀ ሲሆን ሀምሌ 23 በየአመቱ “የመልካምነት ቀን” ተብላ አረጋውያንን በመንከባከብና መልካም በማድረግ የምትታሰብ ይሆናል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል፡፡

በለምለሟ ምስራቅ ጉራጌ ሌላ ገፀ በረከት ተደረበላት።

(ሀምሌ 26/2017 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በክረምት ወራት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ሲያከናውን የቆዬ ሲሆን በዛሬው እለት የባለስልጣኑ አመራርና ሠራተኞች በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ ከ25000 በላይ ችግኞችን ተክለዋል።
በእለቱ ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ ለ100 ተማሪዎች ሙሉ የመማሪያ ቁሳቁስ አበርክተዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰንን ጨምሮ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ከችግኝ ተከላው በኋላ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ኢኮሎጂን ለማስተካከልና የቱሪዝም ምህዳርን ለማስፋት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ያመላከቱ ሲሆን ዞኑ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው በክረምቱ ወራት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ችግኞች ሲተከሉ መቆየታቸዉን ጠቅሰው በዛሬዉ እለትም ከ25000 በላይ ችግኞችን ተክለናል ብለዋል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም ጉራጌ የሰላምና የታታሪነት ተምሳሌት የሆነ ማህበረሰብ መክተሚያ በመሆኗ በዚህ ቦታ አሻራችን በማሳረፋችን ደስ ይለናል ያሉ ሲሆን ችግኞችን ከመትከል በዘለለ የመንከባከብ ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ አመራሮች የትምህርት ቁሳቁሶችን ለተማሪዎች ያበረከቱ ሲሆን ለባለስልጣኑ አመራርም ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተለያዩ ስጦታዎች ተብርክቷል።

አረንጓዴ ዐሻራ ለአለም ምሳሌ የሆንበት ነው ። ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ

(ሀምሌ 24/2017 ዓ/ም)፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የከባቢ ለውጥን በመታደግና የአየር ንብረት ለውጥን በማስተካከል ለአለም ተምሳሌት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል።

ክቡር አቶ አህመድ ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በሸገር ከተማ አስተዳደር  ኩራ ጅራ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በአከናወኑበት ወቅት ነው። ክቡር አቶ አህመድ በንግግራቸው አረንጓዴ አሻራ የምግብ ዋስትናን በማረጋግጥ እና የወጣቶችን የስራ እድል በመፍጠር በኩልም ያለው አስተዋፅዖ የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።

በሌላ በኩል ሸገር ከተማ አስተዳደር ካለው መሬት ውስጥ 30% በአረንጓዴ ተክሎች ለመሸፈን ከ2.8 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር መገባቱን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ አስታውቀዋል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ እንደ ሀገር የተያዘውን በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ አንዱ አካል ሲሆን በእለቱ ከ6000 በላይ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች ተተክለዋል።

በእለቱ ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ ለ1350 ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ እና የ15 አረጋውያን ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የመጣል ስራ የተከናወነ ሲሆን ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለግዥና ንብረት ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ከክቡር ከንቲባው፣ ከአባገዳዎች እና ከአባቶች ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

#GreenLegacy

#700MillionTreesaday!