በኤጀንሲያችን ድረ-ገጽ ላይ በአቅራቢነት በቀላሉ ለመመዝገብ እንዲችሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የአጠቃቀም ማኑዋል (User Guide for Supplier) በቅድሚያ መመልከት እንዳለብዎት አይርሱ፡፡ በመመሪያው መሠረት ምዝገባዎን ያከናውኑ፡፡
በኤጀንሲያችን ድረ-ገጽ ላይ በአቅራቢነት በቀላሉ ለመመዝገብ እንዲችሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የአጠቃቀም ማኑዋል (User Guide for Supplier) በቅድሚያ መመልከት እንዳለብዎት አይርሱ፡፡ በመመሪያው መሠረት ምዝገባዎን ያከናውኑ፡፡
የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከበላይ ኃላፊዎች፣ ከማኔጅመንት አባላት እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር የ2013 የበጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በተመለከተ ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡
በኤጀንሲው ዳይሬክተሮች በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የተከናወኑ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን፣ ትኩረት ሊደረግባቸው ስለሚገቡ ጉዳዮችና ከመደበኛ ሥራ ውጭ ስለተከናወኑ ሥራዎች ከተገልጋይ፣ ከውስጥ አሰራር፣ ከፋይናንስ እና ከመማርና ዕድገት ዕይታዎች አንጻር ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመቀጠልም የኤጀንሲው የበላይ ኃላፊዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች የተሰጡ አስተያየቶችን የተቀበሉ ሲሆን፣ ለተጠየቁ ጥያቄዎችም መልስ በመስጠትና ተጨማሪ ሀሳቦችን በማከል ወይይቱን አሳታፊ አንዲሆን አድርገውታል፡፡
በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ከሠራተኞች አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ጥያቄዎችም ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ለግማሽ ቀን በቆየው የ2013 የበጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በተመለከተ ውይይት ላይ የበላይ ኃላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላት እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የኢፌድሪ የመ.ግ.ን.አ.ኤ.የህዝብ ግንኑነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሰበመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ዙሪያ ከተለያዩ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የግዥ ዳይሬክተሮችና የግዥ አጽዳቂ ኮሚቴ አባላት ከታህሳስ 15-17 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና ሰጠ፡፡
ሥልጠናውን የሰጡት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተሮችና የግዥና ንብረት ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ስለመንግስት ግዥ ምንነት? የመንግስት ግዥ ስለሚመራባቸው ህጎች፣ ስለመንግስት ግዥ መርሆዎች፣ ስለ መንግስት ግዥ አፈጻጸም ተግባርና ኃላፊነት፣ ስለግዥ ሥርዓትና ዑደት፣ ስለጨረታ ሰነድ ዝግጅት፣ ስለመንግስት ግዥ እና ስለመንግሥት ግዥ አጠቃላይ ገጽታ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
በዚህ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና ላይ ግዥና ንብረትን በሚመለከት ለቀረቡት የመወያያ ጥያቄዎች ሠልጣኞች በቡድን በመወያየት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡በዚህ ሶስት ቀናት በቆየው ሥልጠና ላይ ሠልጣኞች የዕውቀት ሽግግርን አግኝተው በሥራቸው ላይ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ ይታመናል፡፡
የኢፌድሪ የመ.ግ.ን.አ.ኤ.የህዝብ ግንኑነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከተለያዩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የተውጣጣ ኮሚቴ በማዋቀር በመንግስት ግዥ አስተዳደር መመሪያ፣ በመንግስት ንብረትና የተሽከርካሪ አጠቃቀም መመሪያ እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በሚመለከት የአምራች ዘርፍ፣ የፋይናንስ ዘርፍ እና የአገልግሎት ዘርፍ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አጠቃቀም መመሪያ ላይ በተከታታይ አምስት ዙሮች በአዳማ ከተማ የማሻሻያ ስራ እያደረገ ይገኛል፡፡
አቶ ወልደአብ ደምሴ የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ በየነ ገብረመስቀል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና አቶ ዳዊት ሽመልስ በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት ወጪ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በጋራ ሆነው በቦታው በመገኘት ለመመሪያ መሻሻያ ኮሚቴነት ለተሳተፉት ባለሙያዎች የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተለያዩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የተውጣጣ በቁጥር 26 ያክል የመመሪያ ማሻሻያ ኮሚቴዎች በግንባታ ግዥ (Procurement Works) እና አለም አቀፍ ግዥን(International Procurement) በሚመለከት በአዲስ አበባ ፍሬንድሺፕ ሆቴል ከመስከረም 2/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ተከታታይ ዙሮች ለመመሪያ መሻሻያ ኮሚቴነት ለተሳተፉት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች ከስልጠናው ለመመሪያ ማሻሻያው ጥሩ የሆነ ግብዓት እንዳገኙ ከኮሚቴዎቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት