የስነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ቀን በደማቅ ስነስርዓት ተከበረ።
(ሕዳር 29/2018 ዓ.ም)፣ የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋምት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛው የሚከበረውን በስሩ የስነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ቀን “ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር’’ በሚል መሪ ቃል አክብረዋል፡፡
በክብረ በዓሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረኩት የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ፍቃዱ ሆሮታ ሲሆኑ በዓሉን ከማክበር በዘለለ ሁሉም ሰው በተሰጠው ሀላፊነት ትርጉም ያለው ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል። ክቡር አቶ ፈቃዱ በዚህ መንግስት ሙስናን ለመከላከል የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝና ትውልድን በስነ-ምግባር በማነፅ በኩልም ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ከስነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ተወከልው የተገኙት አቶ የኋላሸት በበኩላቸው ሙስና ሀገርንም ትውልድንም የሚያቀጭጭና አሳሪ ተግባር በመሆኑ ሁሉም ሊዋጋው ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መልዕክታቸውን ተከትሎ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ማሳወቂያ ሰነድ ለኮሚሽኑ ተወካዮች የማስረከብ ሥነ- ሥርዓት ተካሂዷል።
በዕለቱ የስነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀው ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በጥናታዊ ጽሁፉ ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበውም ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።































