eGP-Ethiopia
2.79K subscribers
1.7K photos
69 videos
11 files
69 links
Download Telegram
3ኛዉ ዙር የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ (e-GP) ሥርዓትን የሚመለከት ስልጠና ተጀመረ።
***
ከመጋቢት 4 እስከ 6/2017ዓ.ም የሚሠጠውና ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ዙሪያ  ኦዲተሮች ያላቸውን ክህሎትና እውቀት የበለጠ አጎልብተው ውጤታማና የዘመነ የኦዲት ተግባራቸውን  ባሉበት ሥፍራ ሆነው እንዲያከናውኑ  የሚያችል  3ኛ ዙር የሲስተም ስልጠና በዛሬዉ ዕለት ተጀምሯል።

በዚሁ ዕለት በተጀመረውና ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ለማሠልጠን በመጡ ባለሙያዎች በሚሰጠው ስልጠና ከተለያዩ የኦዲት የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ከ70 በላይ የፋይናንሽያል ኦዲተሮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

ስልጠናዉ በቀጣይ ዙርም ተጠናክሮ ይቀጥላል።መሰል ተግባሮችን በማከናወን የዘመነ የግዥ ስርዓትን ከማጎለበት ጎን ለጎን የዘመነ የኦዲት ስርዓት በመዘርጋትና ባለሞያዎቹን በማብቃት ጊዜን ቆጥቦ ባሉበት ሆነዉ ኦዲት ማድረግ የሚያስችል ሲስተምን በማሰልጠን ባለስልጣኑ የተሠጠውን ተግባርና ኃላፊነት በቁርጠኝነትና ባለቤትነት ሥሜት እየተገበረ ይገኛል።
Forwarded from Leul Yeneta
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንሆ በአሉበት ትምህርት!
Forwarded from Haile Gebru
Forwarded from eGP-Ethiopia
ከላይ የተቀመጠውን መተግበሪያ (Link) በማስፈንጠር በቀጥታ ሁለቱንም መተግበሪያወች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን።

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን።
የምስጋና እና የሽኝት መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡
*****
የመን
ግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራር እና ሰራተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከጀማሪ ባለሙያነት እስከ ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ለረጅም ዘመን ያገለገሉትንና ለተሻለ መንግስታዊ ተልዕኮ ወደ ሌላ ተቋም የተዛወሩትን ክቡር አቶ ወልደአብ ደምሴን ዛሬ መጋቢት 15/2017 ዓ.ም በክብር ሸኝቷል፡፡

ክቡር አቶ ወልደአብ ደምሴ በመስሪያ ቤቱ በቆዩበት ዘመን በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ላስመዘገባቸው ስኬቶች ግንባር ቀደም መሪ ናቸው፡፡ በተለይም በመሪነት ዘመናቸው ስራን አስተባብሮ በመስራት፣ ችግሮችን በመቅረፍና ሰራተኞችን በመረዳት ረገድ ምሳሌ የሚሆኑና ስራን ሰጥተው ሳይሆን ሰርተው የሚያሰሩ መሪ መሆናቸው በምስጋና እና በሽት መርሃ ግበሩ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ክቡር አቶ ወልደአብ በተለይም “የምታውቁትን ለማያውቁት አጋሩ በቅንነትም ተግባር ላይ አውሉ አሊያ እውቀታችሁ እሳት ሆኖ ያቃጥላችኋል” የሚል መርህ ያላቸውና እውቀታቸውን ሳይሳሱ የሚያካፍሉ በተግባርም የሚያሳዩ መሪ መሆናቸው በሽኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ወልደአብ “ባለስልጣን መሰሪያ ቤቱ የኖርኩበት ቤቴ ነው፡፡ ለግል ጉዳየም ይሁን ለቤቴ የማልሳሳውን ያህል ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ሳልሳሳ አገልግያለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ ውጫዊ ሀይል አስገድዶኝ ሳይሆን ህሊናዬ  አስገድዶኝ የፈጸምኩት ነው” ብለዋል፡፡ ክቡር አቶ ወልደአብ አያይዘውም ተቋሙ ላይ በቆየሁባቸው ዘመናት ሊታለፉ የማይመስሉ ችግሮች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሁሉንም አለፈን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዛሬን ስኬት ተጎናጽፏል፡፡ ይህም በየደረጃው የነበረው አመራርና ሰራተኛ ሚና የጎላ ነበር ብለዋል፡፡

ክቡር አቶ ወልደአብ ተሞክሯቸውን ባጋሩበት ንግግራቸው “እኔ ህይወት አስተምራኛለች፤ተፈጥሮ፣ ጊዜ እና በዙሪያዬ ያሉ ሁሉ አስተምረውኛል፤ እናንተም የህይወትን ትምህርት ኑሩት ብለዋል፡፡ በተለይ መሪዎች ችኩልነትን ማስወገድ፣ ሰከን ብሎ ማሰብን ባህሪ ማድረግ፣ ከህይወት መማርን የህይወት አንድ አካል ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉ መክረዋል፡፡

በሌላ በኩል ተቋማዊ ስርዓት በመገንባት እና ቅንጂታዊ አሰራርን ይበልጥ በማጎልበት ብሎም የተጣለብን ሀላፊነት በቅንነት እና በታማኝነት በመወጣት የተቋሙን ስኬት ማስቀጠል እንደሚገባ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ አሳስበዋል፡፡