በግዥ አፈጻጸምና ንብርት አስተዳደር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በሀገራችን ከሁሉም (ከትግራይ ክልል ዉጪ) ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዥ አፈጻጸምና ንብርት አስተዳደር ዙሪያ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች፤ በወቅታዊ የገበያ ሁኔታ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሐምሌ 23 እና 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለሶስተኛ ዙር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ግልፅ፣ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግስት ግዥ አፈፃፀምና ንብረት አስተዳደር ማስፈን፣ የመንግስትን ንብረት በጥንቃቄ የመያዝ፣ የመጠቀምና የመቆጣጠር እንዲሁም ንብረቱ አገልግሎቱ ሲያበቃ በወቅቱና በተገቢው መንገድ እንዲወገድ ማስቻል ነው፡፡
READ MORE >>