Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

Author: Yonas Habesha

ውጤታማ እቅድ የነገ ብሩህ መንፅር ነው፡፡

(ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም)፣ ለመንግስተ ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ሪፖርት አቀራረብ ስልጠና ተጠናቋል፡፡ ስልጠናው ሁለት ቀናትን የፈጀ ሲሆን የእቅድ አዘጋጃጀት፣ የግምገማ ስርዓትና ሂደት እንዲሁም ሪፖርት አቀራርብ ላይ የሚታዩ ክፍትቶችን ለመሙላትና በእቅድ ላይ የተመሰረት ተግባር ተኮር ውጤት ለማስመዝገብ ታስቦ የተዘጋጄ ነው፡፡

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱትና የስልጠናው አካል የነበሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ሲሆኑ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብና የሚከናወኑ ተግባራት በስኬት እንዲጠናቀቁ እቅድ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም ተቋማዊ ራዕይ እና አላማ ያለ እቅድ ሊሳካ የሚችልበት አግባብ ሊኖር እንደማይችልና የሚታቀድ እቅድም የታቀደበት ስለማይሆን በእቅዳችን ስኬት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፤ ስኬትም ከስኬታማ እቅድ ይመነጫል፡፡ ስለሆነም አሳታፊ እና ፈፃሚን የሚያነሳሳ እቅድ ማዘጋጀተት ብሎም እቅዳችን በየጊዜው መከታተልና መገመገም አሰፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው እቅድ የተቋማዊ ስኬት መልህቅ አሊያም ነገን የምናይበት ብሩህ መንፅር በመሆኑ በትኩረት ልንሰራበት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል እቅድን ማባከን ነገን ማባከን በመሆኑ ትክክለኛ እና እኛን የሚገልፅ እቅድ ማቀድና ክትትልና ግምገማ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ጀማል አህመድ ገልጸዋል፡፡ አቶ ጀማል አክለውም እቅድ የህይወታችን መንገድ በመሆኑ ነገን ስኬታማ ለማድረግ ዛሬ ስኬታማ እቅድ ማቀድ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም እቅድ ማቅድ ብቻውን ስኬት የማያመጣ በመሆኑ የእቅድ ክትትል እና ግምገማ ማካሄድ ብሎም እንደ ተጨባጭ ሁኔታዎች መከለስ የሚያስፈልግ ይሆናል ብለዋል፡፡

ደሜን ለወገኔ የደም ልገሳ መርሃግብር ተከናወነ፡፡

(ሀምሌ 18/2017 ዓ.ም)፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራትኞች በክረምት ወራት ከዋናው ስራቸው ጎን ለጎን የተለያዩ የብጎ አድራጎት ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም በእንጦጦ እና በላፍቶ ለሶስት ጊዜያት የችግኝ ተከላ መርሃግብር ያከናወኑ ሲሆን በዛሬው እለትም “ደም በመለገስ ህይወትን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል የደም በመለገስ መርህግብር አከናውነዋል፡፡

በቀሪ የክረምት ወራትም የችግኝ ተከላ፣ የምገባ፣ አቅመ ደካሞችን የማገዝና ሌሎች የበጎ አድራጎት ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን ይህ የደም ልገሳ መርሃግብርም የክረምቱ የበጎ አድራጎት አንዱ አካል ነው።

“በመትከል ማንሰራራት” የችግኝ ተከላ መርሃግብር እንደቀጠለ ነው፡፡

(ሀምሌ 16/2017 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች  3ኛውን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃግብር በእንጦጦ ፓርክ በተዘጋጀላቸው ስፍራ አከናውነዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌን ጨምሮ ሁሉም አምራርና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በእለቱ ከ2000 በላይ ችግኞችን መትከል ተችሏል፡፡ ይህም እንደሀገር የተያዘውን “በመትከል ማንሰራራት” አንዱ አካል ሲሆን በቀሪ የክረምት ጊዜም የችግኝ ተከላው መርሃግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ ከአለፉት አመታት ጀምሮ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት አረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን (Green Legacy Initiative) ቀርጻ እየተንቀሳሰች የሚገኝ ሲሆን በዚህ የክረምት ወቅትም 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን እንደሚተከሉ ይጠበቃል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናወነ።

(ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማት  አመራርና ሰራተኞች ጋር በመተባበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለ2ኛ ጊዜ አከናውነዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ኢትዮጵያ በያዝነው የክረምት ወቅት 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል አንዱ አካል ሲሆን ተማቋቱ በጋራ ካከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር በተጨማሪ በተናጠልም የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እንደሚኖራቸው ታውቋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ፣ የመንግስት ግዥ አገልግሎት  ዋና ዳይሬከተር ክቡር አቶ  አስማረ ይገዙን እና የሌሎች የገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ  በቀጣይም በክልል ደረጃ ጭምር  በስፋት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።