ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ተደረገ።
(መስከረም 06/2018 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓቱን በማዘመንና ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ዋጋ እንዲያስገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየስራ የሚገኝ ሲሆን አዋጅ ከማሻሻል ጀምሮ የተለያዩ መመሪያዎችንና የአሰራር ማኑዋሎቸነ በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብቷል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለውጡን ለማስቀጠልና የጋራ ለማድረግ እየተገበራቸው የሚገኙ ተግባራትን ለተገልጋዩ ማህበረሰብና ለባለድርሻ አካላትም እያሳወቀ ይገኛል። በዚሀም ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና ከሸሪዓ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮች እና ዳኞች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ በፌዴራል ግዥና ንብረት ባለስልጣን እየተተገበሩ የሚገኙ አበይት የለውጥ ተግባራት በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ለውይይት ቀርቧል። ክብርት ወ/ሮ መሰረት በገለጻቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰፋፊ የለውጥ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን አዋጅ 1333/2016፣ የግዥ አፈጻጻም መመሪያ 1073/2017፣ የመድሐኒትና ህክምና መሳሪያዎች የግዥ መመሪያ ቁጥር1066/2017፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ግዥ መመሪያ 1070/2017፣ የንብረትና ተሽከርካሪ አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1095/2017 ወጥተው መተግበራቸውን አመላክተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ አዋጅን በብሬል ማሳተም፣ የስነ-ምግባር መመሪያ ማዘጋጀትና መተግበር፣ የተገልጋይ ቻርተር ማዘጋጀትና ተግባር ላይ ማዋል እና ሌሎች የለውጥ ተግባራት ተተንትነዋል።
በሌላ በኩል በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በባለስልጣኑ የግዥ ማሻሻያ እና አቅም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ተጓዴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በክብርት ዋና ዳይሬክተሯ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው መርሃ- ግብሩ ፍጻሜውን አግኝቷል።






0 Comments