ውጤታማ እቅድ የነገ ብሩህ መንፅር ነው፡፡
(ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም)፣ ለመንግስተ ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ሪፖርት አቀራረብ ስልጠና ተጠናቋል፡፡ ስልጠናው ሁለት ቀናትን የፈጀ ሲሆን የእቅድ አዘጋጃጀት፣ የግምገማ ስርዓትና ሂደት እንዲሁም ሪፖርት አቀራርብ ላይ የሚታዩ ክፍትቶችን ለመሙላትና በእቅድ ላይ የተመሰረት ተግባር ተኮር ውጤት ለማስመዝገብ ታስቦ የተዘጋጄ ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱትና የስልጠናው አካል የነበሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ሲሆኑ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብና የሚከናወኑ ተግባራት በስኬት እንዲጠናቀቁ እቅድ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት አያይዘውም ተቋማዊ ራዕይ እና አላማ ያለ እቅድ ሊሳካ የሚችልበት አግባብ ሊኖር እንደማይችልና የሚታቀድ እቅድም የታቀደበት ስለማይሆን በእቅዳችን ስኬት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፤ ስኬትም ከስኬታማ እቅድ ይመነጫል፡፡ ስለሆነም አሳታፊ እና ፈፃሚን የሚያነሳሳ እቅድ ማዘጋጀተት ብሎም እቅዳችን በየጊዜው መከታተልና መገመገም አሰፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ መሰረት በንግግራቸው እቅድ የተቋማዊ ስኬት መልህቅ አሊያም ነገን የምናይበት ብሩህ መንፅር በመሆኑ በትኩረት ልንሰራበት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል እቅድን ማባከን ነገን ማባከን በመሆኑ ትክክለኛ እና እኛን የሚገልፅ እቅድ ማቀድና ክትትልና ግምገማ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ጀማል አህመድ ገልጸዋል፡፡ አቶ ጀማል አክለውም እቅድ የህይወታችን መንገድ በመሆኑ ነገን ስኬታማ ለማድረግ ዛሬ ስኬታማ እቅድ ማቀድ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም እቅድ ማቅድ ብቻውን ስኬት የማያመጣ በመሆኑ የእቅድ ክትትል እና ግምገማ ማካሄድ ብሎም እንደ ተጨባጭ ሁኔታዎች መከለስ የሚያስፈልግ ይሆናል ብለዋል፡፡











0 Comments