“በመትከል ማንሰራራት” የችግኝ ተከላ መርሃግብር እንደቀጠለ ነው፡፡
(ሀምሌ 16/2017 ዓ/ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች 3ኛውን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃግብር በእንጦጦ ፓርክ በተዘጋጀላቸው ስፍራ አከናውነዋል።
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌን ጨምሮ ሁሉም አምራርና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በእለቱ ከ2000 በላይ ችግኞችን መትከል ተችሏል፡፡ ይህም እንደሀገር የተያዘውን “በመትከል ማንሰራራት” አንዱ አካል ሲሆን በቀሪ የክረምት ጊዜም የችግኝ ተከላው መርሃግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ ከአለፉት አመታት ጀምሮ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት አረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን (Green Legacy Initiative) ቀርጻ እየተንቀሳሰች የሚገኝ ሲሆን በዚህ የክረምት ወቅትም 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን እንደሚተከሉ ይጠበቃል፡፡






















0 Comments