ከሁሉም የፌደራል ባለበጀት መ/ቤቶች የግዥና ንብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በግዥ አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ የግብዓት ማሰባሠቢያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 1333/2016 የጸደቀውን አዲሡን አዋጅ ማስፈጸም የሚያስችሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያወችን እያዘጋጀ የቆየና ቀደም ሲል የራሱን ሠራተኞች ጨምሮ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት እያወያየ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ የተለያዩ ግብዓቶችን በማሠባሰብ ገንቢ አሥተያየቶችን እየጨመረ ማሻሻያዎችን በማከል አጎልብቶ ተጨማሪ አስቻይና አሠሪ ግብዓቶችን ለመሠብሠብ ስራውን በዋናነት ተግባራዊ ከሚያደርጉት የሁሉም የፌደራል ተቋማት የግዥና ንብረት የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ለመቀበል የተዘጋጀ መድረክ ነው።
መድረኩን የገንዘብ ሚኒስትር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በሥፍራው በመገኘት የከፈቱ ሲሆን የባለሥልጣኑን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት መሥቀሌና ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወልደ አብ ደምሴን ጨምሮ ሁሉም የፌደራል ባለበጀት መ/ቤቶች የግዥና ንብረት የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በመድረኩ እየተሳተፉ ይገኛል።
በአሁኑ ሠዐት ረቂቅ መመሪያው በአቶ አብርሃም ረጋ(የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ባለሞያ) አንድ በአንድ ገለጻ እየተሠጠ ይገኛል። በዋናነት አዲሡ አዋጅ ከነባሩ ያለውን ጉልህ ልዩነት በማሳየትና የተደረጉ መሠረታዊ ማሻሻያዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ላይ የተመሠሰረተ ገለጻ በመስጠት ትኩረቱን ያደረገ ማብራሪያ በማቅረብ መድረኩ ለአሥተያየት በሚያመች መልኩ እየቀረቡ ይገኛል።
ከሠዐት በኋላ ተሳታፊዎች አሥተያየት የሚሠጡበት መርሃግብር እንደሚኖር ይጠበቃል። ግብዓቶችም የተደራጁና ሙያዊ አሥተያየቶች ላይ እንደሚያተኩሩ ይጠበቃል።
በቀጣይ ቀናት ደግሞ የንብረት አሥተዳደር መመሪያው የሚቀርብና በተመሳሳይ ግብዓቶችን የማሠባሠብ መርሃግብር ይኖራል።
1 Comment
Very Nice. I am Abdulkadir from Afar Region Public Procurement and Property Director. organizing such kinds of programs enable every implementer to have a clear understanding of the rules and regulations of procurement and property issue. I kindly request your organization to have similar program with all the regional and city administration peoples.
With Regards
Abdulkadir Kedir