Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ከሁሉም ባንኮችና ኢንሹራንሶች ጋር በኢጂፒ ሲሰተም ትስስር ትግበራ ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ በመክፈቻ ንግግራቸዉ ባለስልጣኑ የዲጅታላይዜሽን እና የትራንስፎርሜሽን ጉዞን ከተቀላቀለ ጊዜ ጀምሮ አሰራርን ዘመናዊ፤ቀልጣፋና ዉጤታማ ለማድረግ በዘርፉ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ተቋም መሆኑን አስታዉሰዉ በተለይም የኢጂፒ ሲስተምን በመጠቀም ቀደም ሲል የተተገበሩና በቀጣይም የተሻሻሉ ትግበራዎችን ጭምር የሲስተሙ አካል በማድረግ ከመተግበር በዘለለ ለንግዱ ማህበረሰብ በኢጂፒ ሲስተም ዙሪያ በቂ መረጃ እንዲኖረዉ በአካል ከሚሰጠዉ ድጋፍ በተጨማሪ በበይነ-መረብ ለመስጠት የሚያሥችል ስርዓት ተጠናቅቆ ወደ ተግባር መገባቱን ጭምር ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡

አያይዘዉም ሲስተሙን ቀደም ሲል ከሌሎች ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ተግባር መከናወኑን ገልጸዉ የዚሁ መድረክ ዋነኛ ዓላማም ባንኮችንና ኢንሹራንሶችን ከመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ጋር ማስተሳሰር መሆኑን በመጠቆም በተለይም ከግዥ ጋር የተያያዙ ማስተግበሪያዎችን ሲስተሙን ተጠቅመዉ የንግዱ ማህበረሰብ (አቅራቢዎች) ደንበኛ ከሆኑበት የትኛዉም የባንክና የኢንሹራንስ አማራጮች በኦንላይን እንዲያዙ የሚስችላቸዉን የሲስተም ዝርጋታ ትዉዉቅ በማድረግ በይፋ ለማስጀመር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የሲስተም ትስስሩ ሁሉም ባንኮችና ኢንሹራንሶች የግዥ ነክ ዋስትናዎችን የኢጂፒ ሲስተምን በመጠቀም ማስቀረብና ማዋቀር እንዲያስችል መደረጉን ጭምር አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም የሲስተም አጠቃቀምን አስመልክቶ ባለስልጣኑ የገጽ-ለገጽም ይሁን የበየነ-መረብ ድጋፍ እንደሚያደርግ በማረጋገጥ ከጥቅምት 1/2017 ጀምሮ የሲስተም ትስስር ትግበራዉ ተፈጻሚ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም የኢጂፒ ፕሮጀክት ዋና ማናጀር አቶ ታደሰ ከበደ በአጠቃላይ የኢጂፒ ትግበራ ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በሙከራ ደረጃ ከተሞከረበት ጀምሮ አሁን የተደረሰበትን ሂደት በመዳሰስ አሳይተዋል፡፡ አያይዘዉም የኢጂፒ ሲስተም አልሚና የፔራጎ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ስራ-አስኪያጅ አቶ እዉነቱ አበራ ባንኮችና ኢንሹራንሶች የሲስተም ትስስሩን እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማያያዝም ጥያቄ፤ሃሳብና አስተያየት እንዲያነሱ ዕድል የተሰጣቸዉ ሲሆን ዕድሉን የወሰዱ ተሳታፊዎች የተፈጠረዉ የሲስተም ትስስር ስርዓት ለማስተዋወቅ የተዘጋጀዉ መድረክ ተገቢ መሆኑን በአዎንታዊ በማንሳት ከተሟላ ቁሳቁስ፤ከደህንነት፤ ከአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሁም ከራሱ ከሲስተሙ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ሃሰሳቦች ያነሱ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎችም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸዉ የፕሮጀክቱ ም/ዋ/ማናጀሮችና ባለሙያዎች ማብራሪያ ሰጥተዉበታል፡፡

በመጨረሻም በባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወልደአብ ደምሴና ዋና ዳይሬክተሯ ክብርት ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ ምላሽና ማጠቃለያ የዕለቱ መርሃ-ግብር ተጠናቅቋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *