የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናወነ።
(ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም)፣ የኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች ጋር በመተባበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለ2ኛ ጊዜ አከናውነዋል።
የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ኢትዮጵያ በያዝነው የክረምት ወቅት 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል አንዱ አካል ሲሆን ተማቋቱ በጋራ ካከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር በተጨማሪ በተናጠልም የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እንደሚኖራቸው ታውቋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ፣ የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬከተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን እና የሌሎች የገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በቀጣይም በክልል ደረጃ ጭምር በስፋት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።






















































0 Comments