የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ከመላው የኤጀንሲው ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡
ክብርት ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የስብሰባው ዓላማ በዚህ በ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የታቀዱ ተግባራት፣የተከናወኑ ተግባራት፣ያልተከናወኑ ተግባራት እና በዕቅድ ተይዘው ያልተከናወኑበት ምክንያት ለመወያየትና በቀጣይ መሰረት ለማስቀመጥ መሆኑን ለውይይቱ ታዳሚዎች ገልጸዋል፡፡በመቀጠልም ወ/ሮ አበባ ዓለማየሁ ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የኤጀንሲውን የ2ዐ11 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት የዕቅድ አፈፃፀምን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ ኤጀንሲው በመጀመሪያው ግማሽ አመት ለማከናወን ያቀደቸውን ማለትም የፈፃሚ ዝግጅትን፣ የተገልጋዮችና ባለድርሻዎችን ዕርካታ ማሳደግ፣የውስጥና የውጭ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት መፍታት፣ የሀብት አጠቃቀምና ውጤታማነት ማጎልበት፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሪፎርም ሥራዎችን ማጠናከር፣ የመንግሥት ግዥ አስተዳደር አፈፃፀምን ማሻሻል፣ ከመ/ቤቶች የሚቀርቡ ዓመታዊ የግዥ እቅዶች በትክክለኛው የጥራት ደረጃ ተዘጋጅተው መቅረባቸውን በመፈተሽ ለመ/ቤቶች ግብረ መልስ መስጠት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የግዥ አፈጻጸም እና ንብረት አወጋገድ አቤቱታዎች እና የጥፋተኝነት ሪፖርቶች ውሳኔ አሰጣጥ ማሻሻል፣ የዘርፈ ብዙ ጉዳዩዮችን በማካተት ተሣታፊነትና ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ የለውጥ ሥራዎችን ውጤታማነት ማሳደግ፣ የሰው ሀብት አቅም ማሳደግ፣ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የሥራ አካባቢ ምቹነት ማሳደግ እና በአጠቃላይ በግማሽ በጀት ዓመቱ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች፣የክትትልና ግምገማ አፈፃፀም፣ያጋጠሙ ችግሮች፣ የመፍትሔ እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚመለከት ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል፡፡