አረንጓዴ ዐሻራ ለአለም ምሳሌ የሆንበት ነው ። ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ
(ሀምሌ 24/2017 ዓ/ም)፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የከባቢ ለውጥን በመታደግና የአየር ንብረት ለውጥን በማስተካከል ለአለም ተምሳሌት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል።
ክቡር አቶ አህመድ ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በሸገር ከተማ አስተዳደር ኩራ ጅራ ክፍለ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በአከናወኑበት ወቅት ነው። ክቡር አቶ አህመድ በንግግራቸው አረንጓዴ አሻራ የምግብ ዋስትናን በማረጋግጥ እና የወጣቶችን የስራ እድል በመፍጠር በኩልም ያለው አስተዋፅዖ የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።
በሌላ በኩል ሸገር ከተማ አስተዳደር ካለው መሬት ውስጥ 30% በአረንጓዴ ተክሎች ለመሸፈን ከ2.8 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር መገባቱን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ አስታውቀዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ እንደ ሀገር የተያዘውን በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ አንዱ አካል ሲሆን በእለቱ ከ6000 በላይ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች ተተክለዋል።
በእለቱ ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ ለ1350 ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ እና የ15 አረጋውያን ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የመጣል ስራ የተከናወነ ሲሆን ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለግዥና ንብረት ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ከክቡር ከንቲባው፣ ከአባገዳዎች እና ከአባቶች ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
#GreenLegacy
#700MillionTreesaday!












