የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ፡፡
የባለስልጣኑ አመራሮችና ሠራተኞች 17ኛዉን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ያከበሩት ከፕላንና ልማት ሚኒሰቴርና ከመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ጋር በጋራ በመሆን ነዉ፡፡
”ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ ነዉ ያከበሩት፡፡
ዕለቱ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ በረከት ፍስሃጽዮን፣የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ፣የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ወልደአብ ደምሴ እና የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ የሆነዉን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር ገላጭ የሆነና ትልቅ ሀገራዊ መልዕክት በማስተላለፍ የጀመረዉ መርሃ-ግብር የሉዓላዊነታችን አርማ ለሆነችዉ ሰንደቅ ዓላማ ለክብሯ ዘብ ለመቆም ቃል በመግባት ቀጥሎ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በጋራ በመዘመር ተጠናቅቋል፡፡