The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ PPS/NVP-1FBI/15/10/2014 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2022
Bid Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሚወገዱ የማያገለግሉ የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች /ኢ-ዌስት/ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር PPS/NVP-1FBI/15/10/2014

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሆኑ የማያገለግሉ የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች /ኢ-ዌስት/ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው እና የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ዝውውር፣ ጊዚያዊ ክምችት፣ የመነቃቀልና ድጋሚ የመጠቀም እንዲሁም የተለዩ ክፍልፋዮችን የማስወገድ ፍቃድ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተሰጠውና የቴክኒክ ብቃት ያለው፣ ለዚህ አገልግሎት የሚውል የተሟላ ወርክሾፕ ያለውና በአካል ማሳየት የሚችል እንዲሁም ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃና መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በመንግስት ግዥ አገልግሎት ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ መንግሥት ግዥ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 007 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
  7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡ የሚወዳደሩባቸውን ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
  9. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድርስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122 37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  13. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት

አዲስ አበባ

 

Bid Attachment

28 10 2014 inovation የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሳ ማስታወቂያ.docx

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 19/07/2022
Bid Closing Time 10:15 am
Expected Award Date19/08/2022
Extended To
Reason for extension