The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ PPPDS/NVP-6FBI/12/07/2013 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2021
Bid Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ የቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPPDS/NVP-6FBI/12/07/2013

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው የገቢዎች ሚኒስቴር አልሙኒየም ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 1,000 ኪሎግራም፣ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 2,000 ኪሎግራም፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 60,000 ኪሎግራም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሣይንስ ኮሌጅ የተለያዩ ቁርጥራጭ ስቲል ብረቶች ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 7,000 ኪሎግራም፣ የብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የተለያዩ ብረታ ብረቶች ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 7‚500 ኪሎግራም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲዛ (ካስት አይረን) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 3‚000 ኪሎግራም እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (steel) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 6,000 ኪሎግራም ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ዝርዝር መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣

4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ መ/ቤት የቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዓይነት ማለትም የገቢዎች ሚኒስቴር አልሙኒየም ብር 9,500.00፣ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ ብር 4,600.00፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ብር 138,000.00፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሣይንስ ኮሌጅ የተለያዩ ቁርጥራጭ ስቲል ብረቶች ብር 12,600.00፣ የብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የተለያዩ ብረታ ብረቶች ብር 18,750.00፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲዛ (ካስት አይረን) ብር 4,500.00 እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (steel) ብር 12,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 007 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

6. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከአገልግሎቱ ጋር ውል መፈራረምና፤ በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የእያንዳንዱ የቁርጥራጭ ብረታብረት ዓይነት ግምታዊ ጠቅላላ መጠን ተወስዶ ባሸነፉበት የ1 ኪሎ ግራም ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም CPO አዘጋጅተው መክፈል አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶቹ ግምታዊ መጠን በርክክብ ወቅት በሚዛን ፕሪንት አውቱ ንባብ ከሚገኘው ትክክለኛ የቁርጥራጭ ብረታ ብረት መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውሉ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት በልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን ከአገልግሎቱ ተመላሽ ሊደረግለት የሚገባ ገንዘብ ካለም በትክክለኛው የገንዘብ መጠን ልክ ሲፒኦ አሰርቶ በመምጣትና በመክፈል ቀደም ሲል ግምታዊ መጠኑ ተሰልቶ ያስያዘው የክፍያ ሲፒኦ በአገልግሎቱ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ፣ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎች በመሸፈን ቁርጥራጭ ብረታብረቱ ከሚገኝበት ሥፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ20 የሥራ ቀናት ዉስጥ ቁርጥራጭ ብረታብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡

11. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122-37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

13. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

አዲስ አበባ

 

Bid Attachment

16 7 2013 PPPDSየተለያዩ የቁርጥራጭ ብረታ ብረት (1).docx

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 07/04/2021
Bid Closing Time 10:00 am
Expected Award Date07/05/2021
Extended To
Reason for extension