The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

Detail Tender Information

Bid No. [ PPPDS/NVP-1FBI/09/05/2013 ]
Procurement Type Goods
Fiscal Year 2021
Bid Description

ክፍል 1 የጨረታ ማስታወቂያ

ንብረትነታቸው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የሆኑ ባህር ዛፎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ጨረታ ቁጥር PPPDS/NVP-1FBI/09/05/2013

አገልግሎታችን ንብረትነታቸው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የሆኑ ባህር ዛፎች በግምት አስር ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚገኘውን አነስተኛ ማገር /ጨፈቃ/፣ መካከለኛ አጣናዎችና ለቋሚና ከዚያ በላይ ሊውሉ የሚችሉ ባህር ዛፎች ቀለም የተቀባውን ሳይጨምር ቀለም በተቀባው ክልል ውስጥ ብቻ ያሉትን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የባህር ዛፎቹን ዝርዝር መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ባህር ዛፎቹን በሱሉልታ ከተማ ቃሶ ወርቢ ቀበሌ በተለምዶ ሚዛን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለው መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ካምፓስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኘተው መመልከት ይችላሉ፣

4. ተጫራቾች ለሚገዟቸው ባህር ዛፎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

6. የባህር ዛፎቹን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ415 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

9. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ተጫራቾች አሸናፊነቱን በተገለጸበት ከ7 /ሰባት/ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል አለባቸው፣ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡

11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃሎ በመክፈል ባህር ዛፎቹን በራሳቸው ወጪ ቆርጠው በ30 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122-37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

13. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

አዲስ አበባ

Description: 468px-Coat_of_arms_of_Ethiopia_svg Description: 468px-Coat_of_arms_of_Ethiopia_svg

CPO /ሲፒኦ

The Federal Democratic Republic of Ethiopia

Public procuremenet and property Disposal Service

ተብሎ ይዘጋጃል

ክፍል 1 የጨረታ ማስታወቂያ

ንብረትነታቸው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የሆኑ ባህር ዛፎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ጨረታ ቁጥር PPPDS/NVP-1FBI/09/05/2013

አገልግሎታችን ንብረትነታቸው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የሆኑ ባህር ዛፎች በግምት አስር ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚገኘውን አነስተኛ ማገር /ጨፈቃ/፣ መካከለኛ አጣናዎችና ለቋሚና ከዚያ በላይ ሊውሉ የሚችሉ ባህር ዛፎች ቀለም የተቀባውን ሳይጨምር ቀለም በተቀባው ክልል ውስጥ ብቻ ያሉትን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የባህር ዛፎቹን ዝርዝር መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ባህር ዛፎቹን በሱሉልታ ከተማ ቃሶ ወርቢ ቀበሌ በተለምዶ ሚዛን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለው መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ካምፓስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኘተው መመልከት ይችላሉ፣

4. ተጫራቾች ለሚገዟቸው ባህር ዛፎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

6. የባህር ዛፎቹን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ415 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

9. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ተጫራቾች አሸናፊነቱን በተገለጸበት ከ7 /ሰባት/ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 /አምስትBid Attachment

ባህር ዛፎች በግልጽ ጨረታ .docx

Mode of procurement NCB
Bid Closing Date 25/02/2021
Bid Closing Time 10:00 am
Expected Award Date25/03/2021
Extended To
Reason for extension