Bid Description |
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
1. ውል ስምምነት ዓላማ፤
ይህ ውል ስምምነት ዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በግዥ ፈጻሚ አካል ወይም ውል ሰጪ እየተባለ የሚጠራ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና ውል ተቀባይ ወይም አቅራቢ ድርጅት ተብሎ የሚጠራ ኢንፊኒቲ አድቨነስድ ቴክኖሎጅ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ለወላይታ ሶዶ ኦቶና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለህክምና አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን ለመግዛት በጨረታ መለያ ቁጥር ግ.ጨ.ወሶዩ 18/2011 በግልጽ ጨረታ ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ.ም ከተወዳደሩ ድርጅቶች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ በዚህ ውል ለተጠቀሱ ዕቃዎች ያቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ (2)ሁለት ዓመት ስታንደርድ ዋራንቲ ተጨምሮ ብር 46,049,550.65 በፊደል (አርባ ስድስት ሚሊዮን አርባ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ብር ከ65/100) ብቻ እና (2)ሁለት ዓመት ስታንደርድ ዋራንቲ አገልግሎት ለመስጠት ውል ስምምነት ከታህሳስ 21 እስከ ሚያዚያ 21/2012 ዓ.ም በአንቀጽ ሁለት በተዘረዘሩ ተክኒክ ፍላጎት መግለጫዎች የተገለጹ የህክምና ዕቃዎችን እና Turnkey Work ለማቅረብ የተደረገ ውል ስምምነት ነው
|