የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለመላው የኤጀንሲው ሠራተኞች የ2007 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ታህሣሥ 29 ቀን 2007 ዓ.ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡
አቶ ጆንሴ ገደፋ የፌደራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በኤጀንሲው ያሉት ዳይሬክቶሬቶች ከመልካም አስተዳደር፣ ከለውጥ ሰራዊት እና ከሕዝብ ክንፍ ውይይት አንፃር ያለፈው 6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሥራ ምን ይመስላል? በሚለው ላይ ለመወያየት መሆኑንና የውይይቱም ተሳታፊዎች ጥያቄ በመጠየቅና አስተያየት በመስጠት በንቃት መከታተልና መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመቀጠልም አቶ አድማሱ ማሞ የለውጥ ትግበራ ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከተገልጋይ፣ ከፋይናንስ፣ ከውስጥ አሠራር፣ ከመማማርና ዕድገት እይታዎች አንጻር በየዳይሬክቶሬቱ በ2007 በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የታቀዱ የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች ላይ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ፋይናንስን በሚመለከት ኤጀንሲው የተመደበለትን በጀት የተገልጋዮችን አቅም ለማገልበትና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት በጀቱን በቁጠባና በአግባቡ በስራ ላይ ለማዋል ትኩረት የሚሰጠው l መሆኑን እና የውስጥ አሠራርን ደግሞ የግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓቱን በማጣጣም ተቀባይነቱን የማሳደግ፣የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን የማሻሻል፣አቤቱታ የማጣራትና ውሳኔ አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም የኤጀንሲውን የሥርዓተ—ጾታ ሥራ መሠራቱን እና የ1 ለ5 አደረጃጀት ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው ዋናው ነገር ተገልጋዮችን ማርካት መሆኑንና ስለአጋጠሙም ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች በማንሳት አስረድተዋል፡፡
በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው የኤጀንሲው የ2ዐዐ7 የመጀመሪያው የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ውይይት ላይ ከ70 በላይ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት