የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለመላው የኤጀንሲው ሠራተኞች የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና እና የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚ/ር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡
አቶ ፀጋዬ አበበ የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን መገምገም፣ የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድንና መደበኛ ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዉ፣ የውይይቱም ተሳታፊዎች ጥያቄ በመጠየቅና አስተያየት በመስጠት በንቃት እንዲተሳፉ አሳስበዋል፡፡
በመቀጠልም የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ አሰራሮችን ከሪፎርምና ከመልካም አስተዳደር ተግባራት ጋር በማስተሳሰር ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ሙስናን የመከላከል ሥነ-ምግባርን በሚመለከት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት በ2ኛው የአምስት ዓመት ስተራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ መሠራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በኤጀንሲው ውስጥ ያሉ የእያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር በተመለከተ የመንግስት ገንዘብ ተመጣጣኝ ዋጋ ማስገኘት እንዲያስችል እና በዘርፉ መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ ግልፅ ፣ፍትሀዊና በውድድር ላይ የተመሰረተ የመንግስት ግዥ አፈጻጸምን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲሁም የመንግስት ንብረት አስተዳደር ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ አሰራሮችን ከተÌማዊ ለውጥና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ጋር በማስተሳሰር ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምን፣ የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድንና የመደበኛ ሥራዎች አፈፃፀምን በአራቱ ዕይታዎች ከተገልጋይ፣ ከፋይናንስ፣ ከውስጥ አሠራር፣ ከመማማርና ዕድገት እይታዎች አንጻርና እንዲሁም ሰለአጋጠሙ ችግሮችና ስለተወሰዱ የማስተካከያ አሰራሮች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎ የጋራ ግንዛቤ ተወስዷል ፡፡
ለአንድ ቀን በቆየው የ2ዐዐ8 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2009 ዕቀድ ውይይት ላይ የኤጀንሲው የበላይ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት