በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረየፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት እና ከኦዲት ቦርድ ሠራተኞች ጋር በመሆን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የፀረ-ሙስናን ቀን ህዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒሰቴር የስብሰባ አዳራሽ አከበረ፡፡ ወ/ሮ ከበቡሽ ሽፈራው በፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልግሎት የስነምግባርና የፀረ- ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባቀረቡት ጽሁፍ ከሙስና ወንጀል ሕጎች ተነስተው ስለወንጀል ምንነት፣ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት መሟላት ስላለባቸው ሁኔታዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች በመንግሥት ሥራ ላይ ሰለሚፈፅሟቸው ወንጀሎች፣ ሌሎች ሰዎች በመንግሥት ሥራ ላይ ሰለሚፈፅሟቸው ወንጀሎች፣ ሰለዝርዝር የሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች፣ በሥልጣን አለአግባብ ስለመገልገል፣ የማይገባ ጥቅም ሰለመቀበል፣ የመንግሥት ሥራን በማያመች አኳኋን ስለመምራት፣ በሥልጣን ሰለመነገድ፣ ያለአግባብ ጉዳይን ሰለማጓተት፣ ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ሰለማግኘት፣በሌለው ሥልጣን ስለመጠቀም ሰፋ ባለ መልኩ አሰረድተዋል፡፡ በመጨረሻም ከፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በሁለት የኤጀንሲው ሰራተኞች ስለ ሙስና ግጥሞች የተነበቡ ሲሆን ለበዓሉም ድምቀትን ሰጥቶታል፡፡ በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸው የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ በፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ.የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
||
|