The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

News

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የ10ኛዉን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርና ከመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጋር በመተባበር ለ10ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ግቢ ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በድምቀት አከበረ፡፡
የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ተ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ  በበዓሉ መክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ፡- “እኛ ኢትዮጵያውያን”  የድህነትና ኋላ-ቀርነት ታሪክ ከሀገራችን ተወግዶ፣ ኢትዮጵያችን በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና በፍጥነት ተራምዳ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ  መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ወደ ማይቀለበስ ደረጃ እንዲደርስ፤ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ለውጥ
በማረጋገጥ ሂደት ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋዎች በማስወገድ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ አላማ ፊት ቃል እንገባለን፡፡ የሚለውን ቃለ- መሐላ በዓሉን ለማክበር ለተሰበሰቡት ሰራተኞች ቃል አስገብተዋል፡፡
በመቀጠልም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በበዓሉ ታዳሚዎች፣በኢትየጵያ የፌደ ራል ወታደሮች እና  በድምፅ በተቀነ ባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመታጀብ ባንዲራውን የመስቀል ሥነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡
ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም የተከበረውን የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የሶስቱም መ/ቤት ሠራተኞች በድምቀት አክብረዋል፡፡
ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ኤጀንሲዉ ከመላዉ ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከመላው የኤጀንሲው ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር በ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በ2010 ዕቅድን በተመለከተ ሃምሌ 11 ቀን 2009 ዓ.ም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡

አቶ ጆንሴ ገደፋ የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት  ኤጀንሲው በ2009 በጀት ዓመት በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ መሆኑና በበጀት ዓመቱ የተከናወኑትን አበይት አፈጻጸሞችን ገምግሞ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቡንና እና ዝቅተኛ አፈጻጸሞችን በመለየት ከመላው የኤጀንሲው  ሰራተኞች ጋር በጋራ በመወያየት አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ የተመዘገቡትን ዝቅተኛ አፈጻጸሞች እና ያጋጠሙትን ችግሮች ለመፍታት ቁልፍ መፍትሄ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የ2010 በጀት ዓመት ዕቅዳችንን በጋራ ማቀዳችንና ለምናከናውነውን ስራ በግልፅና በቆራጥነት እንድንሰራና ወጥ የሆነ የጋራ አመለካከት እንዲኖረን ያደርጋል ብለዋል፡፡

በመቀጠልም በኤጀንሲው ስር የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸማቸውን በአራቱ ዕይታዎች ማለትም ከተገልጋይ፣ ከፋይናንስ፣ ከውስጥ አሠራር፣ ከመማማርና ዕድገት ዕይታዎች አንጻር ዕቅድና አፈፃፀማቸውን በማነጻጸር  ገለፃ  አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ያጋጠማቸውን አንኳር አንኳር የሆኑ ችግሮች፣ ስለተወሰዱ የማስተካከያ እርምቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ዳይሬከቶሬቶቹ አክለውም የ2010 ዕቅዳቸውን ለተሳታፊዎች አቅርበው ሀሳብና አሰተያየት እንዲሰጥበት ተደርጓል፡፡

በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዉ በተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች መልስ እንዲሰጡበት ከተደረገ በኋላ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የማጠቃለያ ንግግር አድርገው የጋራ ግንዛቤ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡ለአንድ ቀን በቆየሁ የዉይይት መድረክ ላይ 110 የሚሆኑ የኤጀንሲዉ ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የመ.ግ.ን.አ.ኤ. ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ የግዥ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከክልልና ከፌዴራል መንግስት ለተውጣጡ ለግዥ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሰኔ 5-9/2009 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሪፍት ቫሊ ሆቴል ስልጠና ሰጠ፡፡
አቶ ጆንሴ ገደፋ የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ተ/ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ በግዥ ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመፍታት የእርስ በርስ ልምድ ልውውጥ በማድረግ የሙያ ክህሎታችንን ለማዳበርና የአቅም ውስንነትና ክፍተታችንን ለመሙላት በእጅጉ ያግዘናል በማለት ስልጠናውን በይፋ ከፍተዋል፡፡
በመቀጠልም በዘርፉ ልምድ ያላቸው የኤጀንሲው የግዥ ባለሙያዎች በተለያዩ የግዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ቀን የተሰጠው ስልጠና ስለ ቁልፍ ውጤታማ የግዥ አመለካቾች (Key Performance Indicators of Procurement) ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ ተደርጎ በጉዳዩ ላይም ለሙከራ ተመርጠው ተግባራዊ ሲያደርጉ የቆዩ አራት ክልሎች ልምዳቸውን በማካፈል አጠቃላይ ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡ በቀሩት አራት ቀናቶችም የመንግስት ግዥ አጠቃላይ ገጽታ፣ የግዥ እቅድና የግዥ ዘዴዎች፣ የጨረታ ሰነድ ይዘት፣ ዝግጅትና ግምገማ ሂደትና የአቤቱታና የጥፋተኝነት ሪፖርት ማጣራት ሂደት ላይ   የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው መጨረሻም የኤጀንሲው ተ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ ስልጠናውን አሰመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው  ስኬታማ እንደነበርና በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው ሁሉም አካል ለመንግስት ገንዘብ ተመጣጣኝ ዋጋ ማስገኘት እንዲችል የበኩሉን አስተዋፅዖ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ በተነሱት ጉዳዮች ዙሪያ ተ/ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ አድርገው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
የመ.ግ.ን.አ.ኤ. ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የግንቦት 20 ድል 26ኛውን ዓመት በዓል በድምቀት አከበረ

የፌዴራል መንግሥት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከመንግሥት የግዥና የንብረት ማስወገድ አግልግሎት ጋር በመተባበር የግንቦት 20 ድል 26ኛውን ዓመት በዓል ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አዳራሽ በድምቀት አከበረ፡፡


አቶ ሰለሞን ዓይኒማር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አግልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር በዓሉን በማስመልከት የሃገራችንን ወደኋላ ያለውን ታሪክና አሁን ያለችበትን ሁኔታ የሚያስረዳ ጽሁፍ የቀረቡ ሲሆን፣ በግንቦት 20 ከተገኙት ትሩፋቶች መካከል ብዝሃነትን ተከተሎ ከተቀረጸው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ዕሴቶች ስለሆኑት ሰለመፈቃቀድ፣  አዲሲቱ ኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የምትገለጽ ሀገር ስለመሆኗ፣ ስለአብሮነትና መልካም ግንኙነት፣ ተደጋጋፊነትና አጋርነት፣ ስለ ሥነ-ልቦናዊ አንድነት፣ ስለመከባበርና መቻቻል ስለ ዲሞክራሲያዊ ዓላማ ማራመድና ሁሉን ነገር በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማሰተናግድ እንደሚገባ በሰፊው አብራርተዋል፡፡
በመቀጠልም የዕለቱ የክብር እንግዶች የሆኑት አቶ ይገዙ ዳባ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አግልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና አቶ ጆንሴ ገደፋ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጊዜያዊ ዋና ዳይሬክተር ስለ ግንቦት 20 ታሪካዊ አመጣጥና ሰለአለፉት ሥርዓቶች አስከፊነት ስለፌዴራላዊ ሥርዓት መገንባት፣ አሁን የት ነው ያለነው? ወዴትስ ነው እየሄድን ያለነው? በሚል ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ የጋራ አገር ስላለን የበለጠ አንድነታችንን እያጠናከርን መሄድ እንዳለብንም አሳሰበዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው የግንቦት 20 ድል 26ኛው ዓመት በዓልን የሁለቱም መ/ቤት ሠራተኞች በድምቀት አክብረዋል፡፡


ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ከንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር ቋሚ የጋራ የምክክር መድረክ ጉባዔ ተካሄደ

በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ከንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና ከክልልና ተቆጣጣሪ አካላት ጋር 7ኛው ዙር ቋሚ የጋራ የምክክር መድረክ ጉባዔ ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አዳራሽ ተካሄደ፡፡
አቶ ጆንሴ ገደፋ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጊዜያዊ ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት በአገራችን የተዘረጋውን የነጻ ገበያ ስርዓት ኢኮኖሚው ከግብርናው መር ወደ ኢንዱሰትሪ መር እንዲራመድ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ከጥቃቅንና አነስተኛ እሰከ ከፍተኛ እንዱስትሪዎች እንደአሸን እንዲፈሉ መደረጉንና ከትናንሽ እስከ ሜጋ የመሰረተ ልማቶችንና ፕሮጀክቶችን ነድፎ ተግባራዊ መሆኑንና ከታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ ባቡርና ሰፋፊ ጎዳናዎች ድረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ በእውነትም ከድህነት ጋር የገጠምነውን ጦርነት በአሸናፊነት እየተወጣን  መሆኑን፣ መንግስትም ለሚያንቀሳቅሳቸው ዘርፈ ብዙ የመሰረተ ልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያገኘው ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የንግዱ ማህብረሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የተለያዩ ሃላፊዎች ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ የአቤቱታና የጥፋተኝነት ሪፖርት ማጣራት ሂደትን በሚመለከት ስለ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት፣ ሰለ አቤቱታ ማጣራት፣ አቤቱታ ሰለማይቀርብባቸውና አቤቱታ ሰለሚቀርብባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፣ ስለ አቤቱታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት፣ በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት የሚካሄድ የአቤቱታ ማጣራት ሂደት፣ የግዥ አፈጻጸምና ንብረት አወጋገድ አቤቱታ አጣሪና ውሳኔ ሰጪ ቦርድ፣ በቦርድ ስለሚከናወን የአቤቱታ ማጣራት ሂደት ያጋጠሙ ችግሮቸና መፍትሄዎቻቸው በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ግዥ አፈጻጸምና ንብረት ማስወገድ አቤቱታ ማጣራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በመንግስት ግዥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በግሉ ዘርፍ እይታን   የመንግስት ግዥ ለምን ትኩረት አስፈለገው? በግዥ አዋጅና መመሪያው የመጡ በጎ ጎኖችና ለውጦች፣ ግልፅነትና ተዓማኒነት ከማስፈንና ፍትሐዊ ተሳትፎን ከማረጋገጥ አንፃር የተካተቱ ለውጦች፣ በግዥ ዙሪያ በአጠቃላይ የሚታዩ ችግሮች፣ በጥናት የተለዩ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸውን በሚመለከት በኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ገለጻ ተደርጓል፡፡
በግዥና ውል አስተዳደር ሰለተከናወኑ ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልግሎት ሰለፈጸማቸዉ ግዥዎች፤ በውል አስተዳደር በኩል የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ሰላጋጠሙ ችግሮች፣ ሰለተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ስለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን በሚመለከት ከመንግስት ግዥና ንብረት ማሰወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በወይይቱ ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አሰተያየቶች የተሰጡ ሲሆን፤ ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ተሰጥል፡፡ለአንድ ቀን በቆየው የምክክር መድረክ ውይይት ላይ የክልል ተቆጣጣሪ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

More Articles...