The FDRE Public Procurement and Property Authority

በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

News

የግዥና ንብረት አስተዳደር የሙያ ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሁለተኛ ዙር ተሰጠ

የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመረውን የግዥና ንብረት አስተዳደር  የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሁለተኛ ዙር በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 27/2010 እስከ ህዳር 23/2010 ዓ.ም. ሰጠ፡፡

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 ዓ.ም. ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከሚያከናውናቸውም ዋና ዋና ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓቱ ወጥነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ የሆነና ግልጽነት የተላበሰ የሙያ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመራ ማስቻል ነው፡፡በመሆኑም 100 ከሚሆኑ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች በBasic level, Essential level & Advanced level በድምሩለ150 ሠልጣኞች ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡ከፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ  በትብብር የተሰጠው ስልጠና ሰለ ግዥ አዋጅ፣  መመሪያ፣ ማኑዋል፣ስለጨረታ ሰነድ እንዲሁም ሰለ  ዓለም ዓቀፍ ግዥ ምርጥ ተሞክሮ፣ ሰለ ግዥ ዘዴዎች፣ ሰለ ግዥ ዕቅድ፣ ሰለ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እርምጃዎች፣ ስለንብረት አያያዝና አጠቃቀም ሰፋ ያለ ስልጠና  ተሰጥቷል፡፡ሰልጣኞችም በቡድን ስራ የተሳተፉ ሲሆን፣ በመጨረሻም የመመዘኛ ፈተና በመስጠት ሶስቱም ደረጃ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሥልጠናው ተጠናቋል፡፡ይህ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ቀጣይነት ያለው ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩትንም የአቅም ክፍተቶች ዘላቂነት ባለው መልኩ ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡

በመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የትምህርት፣ የሥራ ልምድ እና የሙያ ማስራጃዎች የማጣራት ሥራን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

በፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለኤጀንሲው ሠራተኞች በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች የቀረቡ የትምህርት፣ የሥራ ልምድ እና የሙያ ማስራጃዎች  የማጣራት ሥራን አስመልክቶ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የስብሰባ አዳራሽ ጥቅምት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡

አቶ መስፍን መኮንን በኤጀንሲው የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በፌዴራል  መንግሥት  ሠራተኞች የቀረቡ የትምህርት፣ የሥራ  ልምድ  እና የሙያ ማስራጃዎች የማጣራት ሥራን አስመልክቶ በቀረበው ጽሁፍ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫውን የሰጡ ሲሆን፣ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ በርካታ ቀደም ሲል ያልነበሩ  ውስብስብ  ህጋዊ ሳይሆኑ ህጋዊነትን ተላብሰው የሚከናወኑ ተግባራት መከሰታቸው እንደማይቀር እና ይህም አሰራር ሃይ ካልተባለ በሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ህጋዊ አሰራሮች ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡፡
በመቀጠልም ዳይሬክተሩ የውይይቱ ዓላማው ህጋዊ አሰራርን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የተጠያቂነት አሰራርን ማስፈን፣ ቀደም ሲል የተፈፀሙ ህገ-ወጥ አሰራሮችን ማረምና ማስተካከል እና በሒደቱ ተሳታፊ የሆኑ የመንግስት ሠራተኞች እንዲታረሙ እድል ለመስጠት እና በተሰጠው ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ፍቃደኛ ያልሆኑትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡፡

ስለመነሻ ሆኔታዎችም ሲያስረዱ በሀገሪቱ እየተመዘገበ በሚገኘው የኢኮኖሚ እድገት የሲቪል ስርቪስ ሠራተኞች ድርሻ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ሲሆን፣ ነገር ግን አብዛኛው የመንግስት ሠራተኛ ህጋዊ አሰራርን የሚከተል ቢሆንም ቁጥራቸው ቀላላ የማይባሉ የመንግስት ሠራተኞች ሀሰተኛ የትምህርት ፣የሥራ ልምድና የሙያ ማስረጃዎችን በማስያዝ በቋሚ ሠራተኝነት ተቀጥረው ሲሰሩ እንደተገኙ በክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተደረገው የማጣራት ሥራ መረጋገጡንም ገልጸዋል፡፡በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ለግማሽ ቀን በቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ  ውይይት ላይ የኤጀንሲው ሃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

12ኛው የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን እና 29ኛው የኤች.አይቪ. ኤድስ ቀን ተከበረ

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን እና ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጋር በመሆን የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን እና የዓለም አቀፍ የኤድስ ቀን ህዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አዳራሽ በድምቀት አከበረ፡፡

ወ/ሮ እንቁ አሰናቀ ከፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኃላፊ በዓለም ለ27ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ ”በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን መከላከልና ለማስቆም የወንዶች አጋርነትን ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀንን በሚመለከት፣ጾታዊ ጥቃት እና የሴቶች መብት ከሚለው ተነስተው ስለጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭሪቫን/ ንቅናቄ ታሪካዊ አጀማመር፣ የነጭ ሪቫን ንቅናቄ አስፈላጊነት፣ ጾታዊ ጥቃት (violence) ምንድነው? ጾታን መስረት ያደረገ ጥቃትዓይነቶች፣ጾታዊ ጥቃት በማንና የት ይፈጸማል? ስለሚያስከትለዉ ውጤትና የጥቃቱ መንስኤዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡

በመቀጠልም አሰልጣኟ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት አለም አቀፋዊ ገጽታዎች፣ ጾታዊ ጥቃትበኢትዮጵያ፣ስለህግ ማዕቀፍ፣ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት ሴቶች ሊከበሩላቸው ስለሚገቡ መብቶች፣አለም አቀፍ ስምምነቶች፣የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ፣የሲቪል የፍትህ ሥርዓት፣የተለያዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ጾታዊ ጥቃትን መከላከልና ምላሽ መስጠት፣ ወ/ት ትሁት ሙሉጌታ በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን የጤናና ሥነ—ምግብ ፕላን ባለሙያ በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤድስ ቀን በማስመልከት አለምአቀፍ የኤድስ ቀን ማክበር ለምን አስፈለገ?ኤች.አይ.ቪበኢትዮጵያ፣ ስለሶስት ዘጠናዎች ግብ(90-90-90)፣ሰለኤች.አይ.ቪ ስርጭት አሳሳቢነት፣ መቀዛቀዙ ሊያስከፍል ስለሚችለውዋጋ እና ስለትኩረት አቅጣጫዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡ለግማሽ ቀን የቆየው የዓለም የኤድስ ቀን እና የዓለም አቀፍ የጸረ—ጾታዊ ጥቃት ቀን የሶስቱም መ/ቤት ሃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የፌ.መ.ግ.ን.አ.ኤ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት


የግዥና ንብረት አስተዳደር የሙያ ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ለሁለተኛ ዙር ተሰጠ

የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመረውን የግዥና ንብረት አስተዳደር የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠናለሁለተኛ ዙር በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 27/2010 እስከ ህዳር 23/2010 ዓ.ም. ሰጠ፡፡

የፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 649/2001 ዓ.ም. ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ከሚያከናውናቸውም ዋና ዋና ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓቱ ወጥነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ የሆነና ግልጽነት የተላበሰ የሙያ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎችእንዲመራ ማስቻል ነው፡፡

በመሆኑም 100 ከሚሆኑ የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ለተውጣጡ የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎችበBasic level, Essential level & Advanced level በድምሩለ150 ሠልጣኞች ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡

ከፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በትብብር የተሰጠው ስልጠና ሰለ ግዥ አዋጅ፣መመሪያ፣ ማኑዋል፣ ስለጨረታ ሰነድ እንዲሁም ሰለ  ዓለም ዓቀፍ ግዥ ምርጥ ተሞክሮ፣ ሰለ ግዥ ዘዴዎች፣ ሰለ ግዥ ዕቅድ፣ ሰለ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እርምጃዎች፣ ስለንብረትአያያዝናአጠቃቀም ሰፋ ያለ ስልጠና  ተሰጥቷል፡፡
ሰልጣኞችም በቡድን ስራ የተሳተፉ ሲሆን፣ በመጨረሻም የመመዘኛ ፈተና በመስጠት ሶስቱም ደረጃበተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሥልጠናውተጠናቋል፡፡ይህ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Professionalization) ሥልጠና ቀጣይነት ያለው ሲሆን፣ በዘርፉ የሚታዩትንም የአቅምክፍተቶች ዘላቂነት ባለው መልኩ ይፈታል ተብሎ ይታመናል፡፡

በመ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የትምህርት፣ የሥራ ልምድ እና የሙያ ማስራጃዎች የማጣራት ሥራን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

በፌዴራል መንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለኤጀንሲው ሠራተኞች በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች የቀረቡ የትምህርት፣ የሥራ ልምድ እና የሙያ ማስራጃዎች  የማጣራት ሥራን አስመልክቶ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎትየስብሰባአዳራሽ  ጥቅምት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
አቶ መስፍን መኮንን በኤጀንሲው የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በፌዴራል  መንግሥት  ሠራተኞች የቀረቡ የትምህርት፣ የሥራ  ልምድ እና የሙያ ማስራጃዎች የማጣራት ሥራን አስመልክቶ በቀረበው ጽሁፍ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫውን የሰጡ ሲሆን፣ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ በርካታ ቀደም ሲል ያልነበሩ  ውስብስብ ህጋዊ ሳይሆኑ ህጋዊነትን ተላብሰው የሚከናወኑ ተግባራት መከሰታቸው እንደማይቀር እና ይህም አሰራር ሃይ ካልተባለ በሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ህጋዊ አሰራሮች ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡፡
በመቀጠልም ዳይሬክተሩ የውይይቱ ዓላማው ህጋዊ አሰራርን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የተጠያቂነት አሰራርን ማስፈን፣ ቀደም ሲል የተፈፀሙ ህገ-ወጥ አሰራሮችን ማረምና ማስተካከል እና በሒደቱ ተሳታፊየሆኑ የመንግስት ሠራተኞች እንዲታረሙ እድል ለመስጠት እና በተሰጠው ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ፍቃደኛ ያልሆኑትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡፡

ስለመነሻ ሆኔታዎችም ሲያስረዱ በሀገሪቱ እየተመዘገበ በሚገኘው የኢኮኖሚ እድገት የሲቪል ስርቪስ ሠራተኞች ድርሻ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ሲሆን፣ ነገር ግን አብዛኛው የመንግስት ሠራተኛ ህጋዊ አሰራርን የሚከተል ቢሆንም ቁጥራቸው ቀላላ የማይባሉ የመንግስት ሠራተኞች ሀሰተኛ የትምህርት ፣የሥራ ልምድና የሙያ ማስረጃዎችን በማስያዝ በቋሚ ሠራተኝነት ተቀጥረውሲሰሩእንደተገኙ በክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተደረገው የማጣራት ሥራ መረጋገጡንም ገልጸዋል፡፡

በቀረበው ገለጻና ማብራሪያ በተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ለግማሽ ቀን በቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ  ውይይት ላይ የኤጀንሲው ሃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


መ.ግ.ን.አ.ኤ. የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

More Articles...